Logo
TIKVAH-SPORT
“ ያገኘናቸውን እድሎች ብንጠቀም ቢያንስ አቻ እንወጣ ነበር ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድን በዛሬው ጨዋታ የግብ እድሎችን መጠቀም እንዳልቻለ ተናግረዋል።

ከጨዋታው በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት አሰልጣኙ “ ብዙ የግብ እድሎች አግኝተን አልተጠቀምንም “ ብለዋል።

“ ያገኘናቸውን እድሎች ብንጠቀም ባናሸንፍ እንኳን አቻ እንወጣ ነበር “ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

በብሔራዊ ቡድኑ የወሳኝ አጥቂዎች እጥረት እንዳለ እና በዚህ ላይ እንደ ሀገር መስራት እእንደሚገባ ጨምረው ተናግረዋል።

@tikvahethsport      kidusyoftahe
10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.