(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ውስጥ 3 ህንዳዊያን መታገታቸው ተዘገበ፡፡ የህንድ ጋዜጦች ዛሬ ባሰራጩት ዘገባ እንደገለፁት እነዚህ ህንዳዊያን ወደኢትዮጵያ የተጓዙት በህገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደአሜሪካ እንደሚሄዱ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፡፡
የጉጀራት ተወላጅ የሆኑት እነዚህ ህንዳዊያን ኢትዮጵያ ከገቡ በኋላ የት እንዳሉ ሳይታወቅ ደብዛቸው መጥፋቱን የገለፁት ዘገባዎቹ በኋላ ከአዘዋዋሪዎቹ የ1 ክኖር ሩፒ ወይንም የ120,000 ዶላር የቤዛ ጥያቄ እንደቀረበ አስረድተዋል፡፡ በህንድ የሚገኙት ቤተሰቦቻቸው የተጠየቀውን ቤዛ የከፈሉ ቢሆንም ህንዳዊያኑ ግን ላላፉት 3 ቀናት አለመለቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸው ጉዳዩን በአካባቢው ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቃቸውንም አስረድተዋል፡፡
ማንታቪ ኒውስ እንደዘገበው ህንዳዊያኑ ከጉጃራት የተነሱት ሴፕቴምበር 20 ሲሆን ከዚያም በኢትሀድ አየር መንገድ አቡ ዳቢ ተጉዘዋል፡፡ ከዚያም ወደአዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በአዲስ አበባ ጂኤስኤፍ የተሰኘ ገስት ሀውስ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር፡፡ በገስት ሀውሱ ውስጥ ከሴፕቴምበር 20 እስከ 29 ቦታ ተይዞላቸው እንደነበር የጠቀሰው ዘገባው ከሴፕቴምበር 19 እስከ ኦክቶበር 19 የሚያገለግል የኢትዮጵያ ቪዛ እንዳላቸውም አስረድቷል፡፡ ቤተሰቦቻቸው ለዜና አውታሩ እንደተናገሩት ህንዳዊያኑ አዲስ አበባ እንደገቡ በአንድ ኤጀንት አማካኝነት ታግተው ተወስደው ቤዛ የተጠየቀባቸው ሲሆን ቤዛውን ከ3 ቀን በፊት ከፍለዋል፡፡ ነገር ግን እስካሁን የት እንዳሉ ለማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡

10 days ago