(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ላይ "ተጨባጭ መሻሻል" የምታሳይ ከሆነ፣ የማዕቀብ ማቃለያዎችን ለመስጠት እና የታገዱ የገንዘብ ንብረቶቿን ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ለሲኤንኤን ገለጹ።
አደራዳሪዎች ሁለቱን ሀገራት ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ ዋሽንግተን በአደራዳሪዎች በኩል "ገንቢ እና አዎንታዊ ውይይት" እያደረገች መሆኑ ተገልጿል። ሆኖም የኒውክሌሩ ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ካላገኘ ምንም ዓይነት የመጨረሻ ስምምነት እንደማይኖር አጽንዖት ተሰጥቷል። ትራምፕ ባለፈው ቅዳሜ ኢራን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን ዳግም ለመክፈት ያቀረበችውን ሃሳብ "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል ለኢራን ምንም ዓይነት ቅናሽ አላቀረብኩም ሲሉ በይፋ ቢያስተባብሉም፣ "ስምምነት ማድረግ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን እኔ የምፈልገውን ዓይነት ስምምነት አይደለም፤ ዕድላቸውን አባክነዋል" ሲሉ ተናግረዋል። በአሜሪካ በኩል ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትኮፍ፣ ጃሬድ ኩሽነር፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ውይይቱን እየመሩት ይገኛሉ።
በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ዋልትዝ በበኩላቸው፣ ኢራን ያቀረበችው ሃሳብ እምነት የማይጣልበት መሆኑን በመግለጽ፣ ቴህራን አስቀድማ ምንም ዓይነት ተግባራዊ እርምጃ ሳትወስድ ማዕቀብ እንዲነሳላትና የታገደ ገንዘቧ እንዲለቀቅላት ብቻ መጠየቋ ድርድሩን እንዳስተጓጎለው ተችተዋል።

10 days ago