Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
ሜሪት ፕሮፐርቲስ በዲቦራ ፋውንዴሽን የሙያ ስልጠና ማእከል ግንባታ ጀመረ

በሪል እስቴትና በከተማ ልማት ዘርፍ ስሙ እየገዘፈ የመጣው ሜሪት ፕሮፐርቲስ “አንድ ዓመት፣ አንድ ራዕይ ቀጣዩ ምዕራፍ” በሚል መሪ ቃል የአንድ ዓመት የሥራ ጉዞውንና ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አብስሯል።

ኩባንያው የአንድ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን፣ የተገኙ ውጤቶችንና የቀጣይ ዘመን ዕቅዶቹን ያቀረበበት የሚዲያና የባለድርሻ አካላት መድረክ  በዲቦራ ፋውንዴሽን መካሄዱን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡

በተጨማሪም መስከረም 14 በሜሪት ፕሮፐርቲስ እና በዲቦራ ፋውንዴሽን ትብብር የሚገነባው አዲስ የሙያ ስልጠና ወርክሾፕ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ግንባታው 344 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ በአንድ ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ ነው የታቀደው።

ይህ ፕሮጀክት አንድ ሕንፃ ከመገንባት በላይ፣ ክህሎትን ለመገንባት፣ አቅምን ለማጎልበትና የተሻለ የወደፊት ዕድል ለመክፈት የታቀደ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

የሜሪት ፕሮፐርቲስ የሽያጭና ማርኬቲንግ ክፍል ኃላፊ አቶ ምህረቱ ተሰማ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ኩባንያው ባሳለፈው አንድ ዓመት ከ24 በላይ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች ሙሉ ወጪውን በመሸፈን አስገንብቷል።

በተጨማሪም ሜሪት ፕሮፐርቲስ በጥራት፣ በታማኝነትና በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት አማራጮችን በማቅረብ እና የግንባታ ሥራዎቹን በ24 ሰዓት በማከናወን ፕሮጀክቶቹን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።

በቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል
14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.