ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ተመረቀ
አቢሲኒያ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ (አቢሲኒያ ስቲል) በቢሾፍቱ ከተማ የቀድሞ የድርጅቱ ሊቀመንበር የማሄንድራባይ ፓቴል መታሰቢያ "ኤጂአይ" የተሰኘ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ገንብቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ አስረከበ።
ትምህርት ቤቱ የመንግስት የህዝብ ትምህርት ቤት ሆኖ ተማሪዎች በነጻ የሚማሩበት ነው ተብሏል። 380 ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ትምህርት ቤት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በሁለት ፈረቃ እንዲሁም 100 የኬጂ ተማሪዎችን ያስተምራል።
የአቢሲኒያ ግሩፕ ተወካይ አቶ ሄኖክ ደምሰው ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ድርጅቱ ለተማሪዎች ለአንድ ዓመት የምግብ፣ የኬተሪንግ፣ የደህንነትና የጥበቃ ወጪዎችን ይሸፍናል ብለዋል።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጃቲን ፓቴል በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ ለህፃናት የተሻለ የወደፊት እድል የሚገነቡበት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል።
አቢሲኒያ ስቲል በተጨማሪም ለአካባቢው ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።
በትምህርት ቤቱ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ፣ የኬንያ አምባሳደርና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

15 days ago