የሴቶች መስቀል፦ የጉራጌ ሴቶች የክብር በዓል
**********************
የአደይ አበባ ፈክቶ፣ የመስቀል ወፍ ብስራትን ተከትሎ፣ በመስከረም ውብ አየር ውስጥ የጉራጌ ምድር ልዩ ድምቀት ይለብሳል።
መስቀል ለጉራጌ ማኅበረሰብ የበዓላት ሁሉ ዘውድ፣ የታሪክ እና የማኅበራዊ ትሥሥር መገለጫ ነው።
ከዚህ ታላቅ በዓል ጋር በጥብቅ ከተሣሠሩ ውብ ባህላዊ እሴቶች መካከል ደግሞ የመስቀል ዋዜማ ማዕድ የሆነው የጎመን ክትፎ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
በተለይም የ“ሴቶች መስቀል” ወይም “የጎመን ክትፎ ቀን” ተብሎ የእርድ ቀን ከመድረሱ በፊት በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በዓል ድምቀቱ ልዩ ነው።
የመስቀል በዓል ዝግጅት በይፋ በሚጀመርበት በዚህ ዕለት፣ ሴቶች በራሳቸው ወጪ እና አቅም ማዕድ የሚያዘጋጁበት እና በዓሉ በደንብ የሚጎላበት ልዩ ባህላዊ ሥርዓት ይከናወናል።
የጉራጌ ሴቶች ለበዓሉ ካላቸው ታላቅ ክብር እና ፍቅር የተነሣ ወጪውን ለመሸፈን ዓመቱን ሙሉ በገንዘብ እና በግብዓት ይዘጋጃሉ፤ በገንዘብም ሆነ በጉልበት የበዓሉን መሰናዶ ወንዶችን ሳይጨምሩ ሴቶቹ ለብቻቸው ይከውኑታል።
የዕለቱ ዋና ማድመቂያ ደግሞ በጥራት የሚዘጋጀው እና ከቅቤ፣ አይብ እንዲሁም ከጣፋጭ ቅመሞች ጋር የሚታሸው የጎመን ክትፎ ነው።
ለዚህ ማዕድ የሚመረጠው “ሲሟረ” በመባል የሚታወቀው እና እስከ ግንዱ በደቃቁ ተከትፎ የሚዘጋጀው ልዩ የጎመን ዓይነት ነው።
የጎመን ክትፎ የዕለት ተዕለት ምግብ ሳይሆን፣ የክብር እንግዶች በሚሰበሰቡበት፣ የቤተሰብ እና የጓደኝነት ትሥሥር በሚታደስበት ቀን የሚቀርብ የክብር ማዕድ ነው።
በበዓሉ ዕለት፣ የጎመን ክትፎው በቅመማ ቅመም፣ በጥንቃቄ ከተነጠረ እና ከቀለጠ ንጹሕ የላም ቅቤ፣ ሚጥሚጣ እና ኮሮሪማ ጋር ታሽቶ በባህላዊው የሸክላ ዕቃ (ጣባ) ላይ ከቆጮ ጋር ይቀርባል።
ከአይብ ጋር ተቀላቅሎ ወይም ጎን ለጎን ተደርድሮ የሚቀርበው ይህ ማዕድ “ዝማሙጃት” በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ለበዓሉ ልዩ የባህል ግርማ ያላብሰዋል።
የመስቀል ወፍ ብሥራት ይዛ በገባችበት በዚህ ወር፣ የጎመን ክትፎ ማዕድ የጉራጌን ማኅበረሰብ አብሮነት፣ የእናትነት ክብር እና የባህል ባለቤትነት በጥበብ የሚያንጸባርቅ ሀገራዊ ሀብታችን ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ebcdotstream #gurageculture #meskel #ethiopianfood #cultureandheritage

16 days ago