የጨዋታ ቀን
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር በደቡብ ሱዳን ጁባ ናሽናል ስታዲየም ያደርጋል።
ከጨዋታው አስቀድሞ በጁባ ስታዲየም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና አምበሉ ያሬድ ባየህ ዋሊያዎቹ ለድል ሙሉ በሙሉ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እግር ኳስ የዛሬ እንጂ የትናንት ታሪክ አይደለም ያለፈውን ውጤት ወደ ጎን በመተው በ90 ደቂቃው ሙሉ ሦስት ነጥብ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል።
ብሔራዊ ቡድናችን ላለፉት አምስት ዓመታት የሜዳውን ጨዋታዎች ከሀገር ውጭ ሲያደርግ በመቆየቱ ከሜዳ ውጭ መጫወት አዲስ አይሆንበትም።
ይልቁንም በጁባ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ደጋፊዎቻችን ለቡድኑ ትልቅ ተጨማሪ ጉልበት ይሆናሉ ያሉ ሲሆን አምበሉ ያሬድ ባየህ በበኩሉ ቡድናችን ለአንድ ወር ያህል ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
በደቡብ ሱዳን የሚኖረው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና ወንድም የደቡብ ሱዳን ህዝብ የሚያደርጉልንን ድጋፍ ተስፋ በማድረግ የተሳካ ውጤት እንደምናስመዘግብ አንጠራጠርም ብሏል።
ዋሊያዎቹ ትላንት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም የመጨረሻ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በጥሩ የጤንነት እና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

15 days ago