በፈተናዎች የማትናወጥ ሀገር፤ የተቋማት ሪፎርም ለኢትዮጵያ ያጎናጸፈው አስተማማኝ የደህንነት ጋሻ
**********************
ጠንካራና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማት የአንድ ሀገር ቀጣይነት ያለው ልማት ሰላም እና የህግ የበላይነት ዋነኛ ማረጋገጫ በመሆናቸው በሰው ልጅ መለዋወጥ ሳይሆን በተቋማዊ ስርዓት ላይ የተመሰረተ የሀገረ መንግስት ግንባታ በቁርጠኝነት እየተከናወነ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተገበሩ ያሉ የፖለቲካና የልማት እንቅስቃሴዎች አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት እንዲሁም በየአካባቢው የሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተራ የስልጣን ሽግግር ወይም ጊዜያዊ ተግባራት ሳይሆኑ ለትውልድ የሚሻገር ፅኑ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሰፊ የዴሞክራሲ ስርዓት አካል ናቸው።
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በፍጥነት እያደጉ ባሉ ሀገራት ከልማቱ ጋር የተሰናሰሉ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ወሳኝ በመሆኑ የመደመር መንግስት የአሰራር ስርዓትን ማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ማብዛት የዲፕሎማሲና የፈፀመ አቅምን ማሳደግ ላይ አተኩሮ እየሰራ ይገኛል።
የዚሁ መዋቅራዊ የሪፎርም እርምጃ ዋነኛ ማሳያ ደግሞ ሀገራችንን የደህንነትና የፀጥታ ተቋማት ላይ የተከናወነው ስር ነቀል ለውጥ ነው።
ከቅርብ ኣመታት በፊት የነበረው የፀጥታ መዋቅር ለጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን ጥቅም የቆመ በቴክኖሎጂ ወደ ኋላ የቀረና የሀገርን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የመጠበቅ አቅሙ የተገደበ በመሆኑ ለሀገራችን የልማት ጉዞ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።
ይህን ክፍተት በመገንዘብ ሀገራችን የፀጥታ ተቋማቷን መዋቅራዊ ስብጥር የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ አቅም ባሳደገ መልኩ ታሪካዊ የለውጥ ስራዎችን አከናውናለች።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ራሱን በዘመናዊ የመከላከያ መሳሪያዎች፣ ድሮኖች እና ራዳሮች በማደራጀት የምድርና የአየር መከላከያ አቅሙን ያዘመነ ሲሆን በሀገር ውስጥ የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች የሚከናወነው የማምረት ስራ የውጭ ሀገር የትጥቅ ጥገኝነትን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት ሀገራችን በገዛ ልጆቿ እውቀትና አቅም ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ተተኳሽ ጥይቶችን እና ዘመናዊ መሳሪያዎችን ማምረት መቻሏ ለስልታዊ ራስን መቻል ለህዝብ ሰላምና ለኢኮኖሚ እድገት ጠንካራ መሰረት ሆኗል።
በዚህም መሰረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አቅም በመጎልበቱ የዲጂታል ሉኣላዊነትን የማስከበር ሙሉ ብቃት የተገኘ ሲሆን የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትም የተራቀቀ የመረጃ ትንተና ብቃቱን አሳድጓል።
በአጠቃላይ የተከናወኑት ስር ነቀል የተቋማት ሪፎርሞች የሀገርን ሰላም ከማስከበር ባለፈ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱ አለም አቀፍ የሽብር ቡድኖችን ቀድሞ በመመከት ህዝብ ኩራት የሀገር ሉኣላዊነት ጋሻ እና ኢትዮጵያ በፈተናዎች መካከል የማትናወጥበትን የታሪካዊ ጥንካሬ ማማ እውን ያደረጉ ናቸው።
በብሌን ደምበሎ

18 days ago