Logo
FBC
የመስከረም ህብረ ቀለማት፤ ከባህላዊ እሴት እስከ ሀገራዊ ማንሰራራት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች የተገነባችውና የብዙሃን ማንነቶች መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ በየዓመቱ የምትቀበለው የመስከረም ወር የብሩህ ተስፋ ማብሰሪያ በመሆን በህዝቦቿ ዘንድ ልዩ ቦታ ይይዛል።

ይህ ወቅት የአየር ንብረት መለወጥን ብቻ ሳይሆን፤ ማህበራዊ ውህደትን፣ ይቅር ባይነትን፣ የአብሮነትንና የሀገራዊ አንድነት ትርክት በጉልህ የሚያደምቁ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት መሰብሰቢያ ነው።

ኢትዮጵያውያን ዘመናት ከተሻገሩ ጥንታዊ ባህሎቻቸው መካከል የሰላም፣ የመደጋገፍ እና የግጭት መፍቻ እሴቶቻቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። እነዚህ እሴቶች ማህበራዊ ፍትህንና ሰላምን ለማረጋገጥ የሚረዱ ሀገር በቀል አስተዳደራዊ ጥበቦች ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በያዘችው የሀገር መንግሥት ግንባታ እና የማንሰራራት ምዕራፍ ውስጥ እነዚህን ነባር ባህላዊ እሴቶች መንከባከብና ማጠናከር ወሳኝ ጉዳይ ነው።

በቅርቡ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር የዚሁ እሴት ነጸብራቅ ሲሆን፤ ከተለያዩ ማህበረሰቦች የተወጣጡ ሀገራዊና ባህላዊ አሰራሮች፣ በህዝቦች መካከል የነበሩ የቆዩ ቅሬታዎችን ለመፍታትና የጋራ መግባባትን ለመፍጠር መንገዱን አቃንተውታል።

እነዚህ የማይደሰሱ የባህል ቅርሶች ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍና ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በጽኑ መሰረት ላይ የተተከሉ ዋና ዋና ምሰሶዎች ናቸው።

የቱሪዝም ልማት ነባር እሴቶችን ጥሎ የሚሄድ ሳይሆን፤ ህዝቡ በራሱ ባህላዊ አስተዳደርና እሴቶች እየተጠቀመ ሀገራዊ እድገቱን የሚያፋጥንበት መንገድ ነው።

ኢትዮጵያ ወደተቀመጡት ግዙፍ የልማትና የእድገት ህልሞች ለመጓዝ አስቀድሞ ሰላም፣ መተማመንና የህዝቦች ወንድማማችነት ያስፈልጋታል።

የጋራ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ወደ ፖለቲካው ስርዓት ሲመጣ በዜጎችና በመንግሥት መካከል ያለው መተማመን ይጎለብታል።

ስለሆነም በመስከረም ወር ጎልተው የሚወጡት የመደጋገፍና የመቻቻል እሴቶች፣ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ እንዲሁም ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፈተናዎችን በአንድነት ለመሻገር ትልቅ አቅም ይሆናሉ።

በዮናስ ጌትነት

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.