Logo
SeledaPost
በቅጠል ተራ በ4 ወራት የተገነቡ 960 የመኖሪያ ቤቶች ለአካባቢው ነዋሪዎች ተላለፉ

​በአዲስ አበባ ከተማ ቅጠል ተራ አካባቢ በ4 ወራት ውስጥ የተገነቡ 960 የመኖሪያ ቤቶችና 371 የንግድ ሱቆች ከቦታው ለተነሱ ነዋሪዎች መተላለፋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ቀደም ሲል ለኑሮ ምቹ ያልነበረውና በተደጋጋሚ የእሳት አደጋ ይደርስበት የነበረው ይህ ስፍራ፣ አሁን "የመርካቶ የበጎነት መንደር" በሚል ተሰይሟል።

​በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ 9 ዘመናዊ G+8 ብሎኮች፣ የሕፃናትና ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣ የውስጥ አስፋልትና ሊፍት ተሟልተውላቸዋል።

ይህ ፕሮጀክት በመርካቶ የሚገኙ የተለያዩ «ተራ» አካባቢዎችን ዘመናዊ የማድረግ ሥራ አካል ነው ተብሏል።

Seledadotio
Seledadotio
16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.