Logo
YenetaTube
በተቀጠረች በመጀመሪያ ቀን የሞባይል ስልክና አልባሳትን የሰረቀችው ግለሠብ በእስራት ተቀጣች።

በምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ ውስጥ በተቀጠረች የመጀመሪያ ቀን ከተቀጠረችበት ቤት የስርቆት ወንጀል የፈፀመችው ግለሠብ በእስራት መቀጣቷን የጊኒር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምርመራ ክፍል አስታውቋል፡፡

የከተማው ፖሊስ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር አማን ቲቤሶ እንደተናገሩት ተከሳሽ ደራርቱ ገመዳ የተባለች የሃያ አምስት ዓመት ተቀጥራ ለመስራት ከገባችበት ቤት ሁለት የእጅ ስልኮችና አልባሳትን በሻንጣ ሞልታ ልትሠወር ስትል በቁጥጥር ስር ውላለች።

ተከሳሿ መስከረም 5ቀን 2019 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ሲሆን አሰሪዋ ከቤት ስትወጣ ጠብቃ መኝታ ቤትዋ በመግባት አይፎን ፕሮማክስ እና ሳምሰንግ A 10 የተባሉ ሁለት የእጅ ስልኮችን፣ የተለያዪ የሴቶች አልባሣት እና የመዋቢያ ቁሣቁሶችን በሻንጣዋ ውስጥ አድርጋ በአንድ ሆቴል የመኝታ ክፍል ተከራይታ እንደተሸሸገች ተገልጿል።

የቤቱ ባለቤቶች ከሔዱበት ሲመለሱ መኝታ ክፍላቸው ተከፍቶ ንብረታቸው መዘረፉን በመረዳታቸው ወዲያው ለፖሊስ ያመለክታሉ።ፖሊስም የደረሠውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ከምሽቱ አራት ሠዓት ላይ እራስዋን ለመለወጥ ተከናንባ ለብቻዋ ስትዝናና በምሽት የፖሊስ ጥበቃ አባላት በቁጥጥር ስር ልትውል ችላለች፡፡

የጊኒር ከተማ ፖሊስም ተከሳሿን በቁጥጥር ስር በማዋል በአስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥባት የምርመራ መዝገቡን በተለያዪ ማስረጃዎች በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቢ ሕግ አስተላልፋል።አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የስርቆት ወንጀል ክስ መስርቷል።

ክሱን የተመለከተው የጊኒር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መስከረም 7ቀን 2019 ዓም በዋለው ችሎት ተከሣሽ ደራርቱ ገመዳ፣የቤት ሠራተኛ ሆና ስራን ምክኒያት በማድረግ በአሠሪዋ ላይ ስርቆት መፈፀምዋ በማስረጃ አረጋግጧል።በዚህም መሰረት በ5 አመት ከ5 ወራት እስራት እንድትቀጣ የተወሠነባት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር አማን ቲቤሶ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

Via ዳጉ_ጆርናል

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.