(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ የሙዚቃ እና የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፈው ታዋቂው ባለሙያ ግርማ ነጋሽ፣ ባጋጠመው የጤና እክል በመኖሪያ ቤቱ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በ83 ዓመቱ ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ገደማ ሕይወቱ አልፏል።
በ1936 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ፊት በር አካባቢ የተወለደው ጋሽ ግርማ፣ በፖሊስ ኦርኬስትራ እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ ብሔራዊ ቲያትር) ለበርካታ ዓመታት አገልግሏል። «ምነው ተለየሽኝ»፣ «የኔ ሀሳብ»፣ «እንገናኛለን» እና «አልበቃኝም ገና» የተሰኙት ተወዳጅ ዜማዎቹ የዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ ናቸው። ከሙዚቃው ዓለም ባሻገር በስፖርት ጋዜጠኝነቱ፣ እንዲሁም በታላቅ የሰው አክባሪነት ስብዕናው በቅርብ በሚያውቁት እና በአድናቂዎቹ ዘንድ ምንጊዜም ሲታወስ ይኖራል።
የሶስት ወንዶች እና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የነበረው የጋሽ ግርማ ነጋሽ ሥርዓተ ቀብር ነገ ከቀኑ 5:00 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍስ ይማር!

15 days ago