(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ (ዲ.ኤም.ቪ) የሚገኙ የወላይታ ብሔር ተወላጆች፣ የብሔሩ አሮጌው ዓመት መሸኛ እና የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የዘመን መለወጫ ‘ጊፋታ’ በዓል ከሦስት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በቨርጂኒያ ግዛት በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።
በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወላይታ የመጨረሻ ንጉሥ የሆኑት የንጉሥ ጦና አራተኛ ትውልድ ወ/ሮ ሪብቃ ደስታ ፍሰሃ (ሮቤ ጦና)፣ ጊፋታ ከጊዜ አቆጣጠርነቱ ባሻገር የወላይታ ሕዝብ የስልጣኔ መነሻ፣ የአንድነት፣ የመሰባሰብ እና የፍቅር ተምሳሌት በመሆኑ የተለየ ክብር እና ሞገስ እንደሚሰጠው ገልጸዋል። የአባቶችን ታላቅነት እና አይበገሬነት ለትውልድ ማስተላለፍ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ያሳሰቡት ወ/ሮ ሪብቃ፤ ከ36 ዓመታት በፊት በፖለቲካ ጥገኝነት በሰሜን አሜሪካ ቆይተው ያረፉት አባታቸው ፊታውራሪ ደስታ ፍሰሃ፣ ይህንን ታላቅ የሕዝብ ስብስብ እና ፍቅር ቢያዩ ምን ያህል ደስ ባላቸው ነበር ሲሉ ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት ተናግረዋል።
የዘንድሮውን በዓል ለየት ካደረጉት ሁነቶች መካከል በወጣት ኢንጂነር ሳምሶን ራማቶ የተዘጋጀው የወላይታ ብሔር ዲጂታል የዘመን አቆጣጠር (Gifaataa Digital Calendar) ይፋ መደረጉ ነው። ወጣቱ የብሔሩን የዘመን ቀመር ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማሸጋገር ላደረገው የላቀ ጥረት ከታዳሚው ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና የተቸረው ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ይህንን የዘመን አቆጣጠር በጎግል ክሮም (Google Chrome) መፈለጊያ ላይ "Wolaita. netlify .app" ብለው በመጻፍ ማግኘት እንደሚችሉ በዕለቱ ተገልጿል።
ዝግጅቱ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንዲሁም አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ባህላዊ ጭውውቶች የቀረቡበት ነበር። ታዳሚው ልዩ ልዩ ባህላዊ ምግቦችን (የጥሬ ሥጋ ቁርጥ በዳታ አዋዜ፣ ቆጭቆጮ፣ ቡላ እና የመሳሰሉትን) እየተመገበ በዓሉን ያከበረ ሲሆን፣ የዕለቱ መርሃ ግብር በሴቶች የ‘ኩላ ኩርቹቼ’ እና በወንዶች የ‘ባልሄሌሌ’ ባህላዊ ጨዋታዎች በድምቀት ተጠናቋል።
ይህ የዘንድሮው የጊፋታ በዓል፣ ትውፊቱ ከባህላዊ አልባሳቱ (ዱንጉዛ ሀዲያ)፣ ምግቡ እና አጨዋወቱ ጋር በመሆን እ.ኤ.አ. በ2025 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) በማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች (Intangible Cultural Heritage of Humanity) ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገበ በኋላ የተከበረ የመጀመሪያው በዓል በመሆኑ ታሪካዊ ፋይዳው የጎላ ሆኗል።
(ዘገባው ለዘ-ሐበሻ - በሙሉቀን ገብሬ ላንካ ከዲ.ኤም.ቪ ወላይታ ኮሚዩኒቲ የተጠናቀረ ነው)

15 days ago