(ዘ-ሐበሻ ዜና) የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኒውዮርክ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከተወያዩ በኋላ፣ የዓለምን የኃይል (ኢነርጂ) ገበያ ለማረጋጋት እና ለግጭቶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ።
ማክሮን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መግለጫ ኒውዮርክ እንደደረሱ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ዙሪያ የጋራ ምላሽ ለመስጠት መምከራቸውን ገልጸዋል። የፈረንሳዩ መሪ አክለውም፣ "በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በማስጠበቅ እና በሆርሙዝ ስትሬት የባህር ላይ ጉዞ ነጻነትን በማረጋገጥ፣ በኃይል ገበያው ላይ ያለውን ውጥረት ለማርገብ በጋራ ለመስራት ወስነናል" ብለዋል።
ከመካከለኛው ምስራቁ ውጥረት ባሻገር የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትም የውይይቱ አካል ነበር። ሁለቱ መሪዎች በዩክሬን የኃይል እና የሲቪል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እንዲቆም (Moratorium እንዲደረግ) የጋራ ጥረታቸውን እንደሚያስተባብሩ ማክሮን አስታውቀዋል። "የሲቪል ማህበረሰቡ ከጥቃት ሊጠበቅ ይገባል፤ እንዲሁም በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ለሰላም የሚያበቃ ከባድ እና እውነተኛ ድርድር በተቻለ ፍጥነት ልንጀምር ይገባል" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።
በአንድ በኩል ማክሮን ትራምፕን አግኝተው ስለ ሆርሙዝ ስትሬት እና ስለ መካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ መሰረተ ልማት ደህንነት አብዝተው መምከራቸው፣ የቀጣናው ኃይሎች (በተለይም ኢራን እና ሁቲዎች) በዓለም የኢኮኖሚ የደም ስር ላይ የደቀኑትን አደጋ በጉልህ ያንጸባርቃል። አውሮፓ ያለ አሜሪካ ወታደራዊ ጥላ ይህንን የኃይል መስመር ማስጠበቅ እንደማትችልም በግልጽ ያሳያል።
በሌላ በኩል ፈረንሳይ (የአውሮፓ ህብረትን በመወከል) የዩክሬንን የሰላም ድርድር በተፋጠነ ሁኔታ ለመጀመር ከአሜሪካ ጋር መግጠሟ፣ የጦርነቱ ጫና በምዕራባውያን ኢኮኖሚ ላይ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ህያው ምስክር ሆኖ ይቆማል። ይህም የትራምፕ አስተዳደር በዩክሬን ጦርነት ላይ ያለውን "ጦርነቱ በአፋጣኝ በድርድር ማለቅ አለበት" የሚል ፖሊሲ፣ አውሮፓውያን በውድም በግድም እየተቀበሉት እና ስትራቴጂያቸውን እያስተካከሉ መሆኑን ያመላክታል።

17 days ago