Logo
Getu Temesgen
ተከታዮቹ ከጋና ህዝብ የሚበልጡት ዩቱበር መንደር መሠረተ
#ethiopia | ​ታዋቂው ዩቲዩበር ሚስተር ቢስት በጋና 10 ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጪ እጅግ ዘመናዊና አጠቃላይ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ያካተተ መንደር በመገንባት የሚያስመሠግን የበጎ አድራጎት ስራ አከናውኗል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት 10 ክፍሎች ያሉት ትምህርት ቤት፣ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ የነጻ ምግብ አቅርቦት፣ የጤና ክሊኒክ፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ የሶላር ኃይል፣ የገበያ ማዕከል እና ለመምህራን የሚሆኑ 10 ነጻ የመኖሪያ ቤቶችን ያካተተ ነው።

​ይሁን እንጂ የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ስኬት ሚስጥር አዳዲስ ህንጻዎችን በመገንባት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ የማህበረሰቡን መሰረታዊ ችግሮች በጥቅሉ በመቅረፍ ላይ ያተኮረ ነው።

ለምሳሌ በድሮው ትምህርት ቤት የነበሩ 325 ተማሪዎች በዝናብ ወቅት በመንገዶች መጎርጎር ምክንያት ወደ ክፍል ለመግባት ይቸገሩ የነበረ ሲሆን፣ የቡድኑ አባላት አነስተኛ የነበረውን የውሃ ማፍሰሻ ቧንቧ በትልልቅ የውሃ መውረጃዎች በመተካት ያንን መሰናክል በቀላሉ አስወግደዋል።

ትምህርት፣ ምግብ፣ ንጹህ ውሃ እና የጤና አገልግሎት በአንድ ላይ ሲሟሉ የሰዎችን እድገት የሚያደናቅፉ መሰናክሎች ሙሉ በሙሉ እንደሚወገዱ የሚያሳየው ይህ ፕሮጀክት፣ አንዳንዴ ትልቅ ለውጥ የሚጀምረው ትንንሽ መሰናክሎችን በጥበብ በማስወገድ እንደሆነ በተግባር አስመስክሯል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.