Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አሜሪካ በሱማሊያ ለተሰማራወ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ የምታደርገውን ድጋፍ ለአንድ አመት ለማራዘም ወሰነች፡፡ የአሜሪካ መንግስት በሱማሊያ ለሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ የሚሰጠውን ድጋፍ በአንድ አመት ማራዘሙን ሮይተርስ ዘገበ፡፡ እንደዘገባው ከሆነ አሜሪካ ድጋፉን የምትሰጠው በቀጥታ ለሰላም አስከባሪው ሀይል ሳይሆን በሱማሊያ ለሚገኘው የተመድ ድጋፍ ሰጭ ቢሮ ነው፡፡ ይህም ቢሮው ለሰላም አስከባሪው ሀይል እያቀረበ ያለውን የሎጅስቲክ ድጋፍ ለሚቀጥሉት 12 ወራት እንዲሰጥ የሚያስችለው ይሆናል፡፡ ቢሮው ቀደም ሲል የበጀት እጥረት ስላጋጠመው ይህንን ድጋፍ ለማቆም መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህ የተነሳም በሱማሊያ የሚገኙት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች አገሪቱን ለቀው መውጣት መጀመራቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ቢሮው አመታዊ በጀቱ ወደ500 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ትልቁን ገንዘብ የምታዋጣው አሜሪካ ናት፡፡ የአሜሪካ መንግስት ከጥቂት ወራት በፊት ይህንን ወደ190 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ መዋጮ ለማቆም ወስኖ የነበረ ሲሆን ይህ እርምጃው አሁን አቋሙን መለወጡን የሚያሳይ ነው፡፡

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.