ዴንማርክ አሜሪካ በግሪንላንድ ደሴት ላይ "ዘላቂ ቁጥጥር" እንዲኖራት የሚያስችል አስገዳጅ የደህንነት ስምምነት መደረጉን በበጎ መቀበሏን አሳወቀች።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በደሴቲቷ ጉዳይ ላይ የተደረሰው ስምምነት ዘላቂ መሆኑንና አሜሪካ በአካባቢው ያላትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወዲያውኑ ማሳደግ እንደምትጀምር ገልጸዋል።
ስምምነቱን ተከትሎ እንደ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ የአሜሪካ ተፎካካሪዎች ያለ ዋሽንግተን የጽሑፍ ፈቃድ በግሪንላንድ ወታደራዊ ጣቢያ መክፈት፣ ወታደር መላክ ወይም ኢንቨስት ማድረግ አይችሉም ተብሏል።
ስምምነቱ በሚቀጥለው ሳምንት በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በይፋ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
የዴንማርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜቴ ፍሬደሪክሰን ስምምነቱ የዴንማርክን የግዛት ሉዓላዊነት እና የግሪንላንድን ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ያከበረ ነው ብለዋል።
የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ሎኬ ራስሙሰን በበኩላቸው ስምምነቱ በአርክቲክ እና በሰሜን አትላንቲክ ቀጠና ያለውን ደህንነት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
አሜሪካ በሰሜን ግሪንላንድ ካላት የፒቱፊክ ወታደራዊ ጣቢያ በተጨማሪ በደቡባዊ የደሴቲቱ ክፍል ሶስት አዳዲስ ወታደራዊ ጣቢያዎችን ለመክፈት አቅዳለች።
ስምምነቱ ከዚህ ቀደም ትራምፕ ግሪንላንድን በኃይል ለመውሰድ መዛታቸውን ተከትሎ በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባላት መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ከፍተኛ ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ይገመታል።
DW Amharic #amharicmezmur

20 days ago