የመደመር ትውልድ ቁጭት፡- ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የማሸጋገር ራዕይ
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ከኢትዮጵያ እኩል የስልጣኔን መንገድ ከጀመሩት ሀገራት ጋር ስንነጻጸር ሀገራችን ለምን ወደኋላ ቀረች? የሚለው ጥያቄ የመደመር ትውልድ አቢይ ቁጭት ነው።
ሩሲያ እና ቻይና ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዜጎቻቸውን በቅጡ መመገብ ባልቻሉበት አስቸጋሪ ጊዜ የኒውክሌር እና የጠፈር ሳይንስ ቴክኖሎጂን ሲጀምሩ፣ ሀገራችን ግን የመጀመሪያውን የኢንዱስትሪ አብዮት ለመቀላቀል የሚያስችል አቅም ቢኖራትም በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሳይሳካ ቀርቷል።
በጋዝና በነዳጅ የበለጸጉ ሀገራት ዜጎቻቸውን ወደ ምቾት ሲያሸጋግሩ፣ ሀገራችን ግን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የተቆፈረውን ጉድጓድ እንኳን ወደ ሀብትነት መቀየር ሳትችል ዘመናትን አሳልፈናል።
የዓለምን የኢኮኖሚ ከፍታ የተቆናጠጡት እንደ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጀርመን ያሉ ሀገራት ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ዕድገታቸው ከድህነት እና ከውድቀት በኋላ በተፈጠረ ጠንካራ ሀገራዊ ቁጭት ላይ የተገነባ መሆኑን እንረዳለን።
ቻይናውያን የመቶ ዓመት የውርደት ታሪካቸውን በከፍተኛ የሥራ ትጋት ቀይረው የዛሬዋን ልዕለ ኃያል ሀገር ሲፈጥሩ፣ ኮሪያውያን ደግሞ በአስቸጋሪው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ወቅት የግል የወርቅ ጌጣቸውን ሳይቀር ለመንግሥት በማበርከት ሀገራቸውን ከብሔራዊ ኪሳራ ታድገዋል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየው ሀገራት ወደ ከፍታ የሚወጡት ዜጎቻቸው ለነገው ትውልድ ሲሉ ዛሬ ላይ የጨከነ መስዋዕትነት ለመክፈል ሲወስኑ መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያችንም የትናንት ትውልድ በደም መስዋዕትነት ሀገርን አጽንቶ ያቆየ ሲሆን፣ የዛሬው ትውልድ ደግሞ ሀገሩን ከድህነት ለማላቀቅ "የላብ መስዋዕትነት" ሊከፍል ግድ ይለዋል።
ይህ የላብ መስዋዕትነት የሚገለጠው እያንዳንዱ ዜጋ በተሰማራበት የሙያ መስክ በከፍተኛ ኃላፊነት፣ ተነሳሽነት እና ጽናት ሥራውን ሲያከናውን ነው። ለተተኪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ የዛሬን ምቾት መስዋዕት ማድረግና የተሰጠን ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት ያስፈልጋል።
ሀገራዊ መግባባትን እና ሰላምን መሠረት አድርጎ በአንድነት በመቆም ብሔራዊ አጀንዳዎችን ከዳር ማድረስ፣ ኢትዮጵያን ከታሪክ ተናጋሪነት ወደ ታሪክ ሠሪነት የሚያሸጋግራት ብቸኛው እና አስተማማኙ ጎዳና ነው።
ይሁን እንጂ ዛሬ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ሀገራችን ከጥልቅ እንቅልፍ ነቅታለች። የትናንቱን የጉስቁልና ልምምድ የሚጠየፍ እና የተሻገረ አስተሳሰብ ያለው የመደመር ትውልድ፣ የብልጽግናን ማማ ለመውጣት እንቅልፍ አልባ ጉዞ ጀምሯል።
መዝለልን እሳቤ በማድረግ እንደ አቦሸማኔ ለመፍጠን የቆረጠችው ኢትዮጵያ፣ ማንም በምንም ሁኔታ የማያስቆማት አዲስ የለውጥ ሪቫን ቆርጣለች።
በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በራሷ አቅም የገነባችው ኢትዮጵያ፣ አፍሪካውያን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማስተዳደር አይችሉም የሚለውን የተሳሳተ ትርክት በመስበር የኢኮኖሚ ዓድዋዋን ተቀዳጅታለች።
ይህ የሕዳሴው ግድብ ስኬት ለሀገራችን የሜጋ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ ሞተር ከመሆኑም በላይ አሁን ላይ አምስት እና ስድስት ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በአንድ ጊዜ በልበ ሙሉነት ለማስጀመር አቅም ፈጥሮላታል።
በተለይም በሶማሌ ክልል የተገኘው የተፈጥሮ ጋዝን ጨምሮ በመሠረተ ልማት፣ በኢነርጂ አቅርቦት እና በግብርና ምርታማነት ላይ ያተኮሩት እነዚህ የልማት ውጥኖች ተጠናቅቀው ወደ ሥራ ሲገቡ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መዋቅር እና የሕዝቧን የኑሮ ገጽታ ሙሉ ለሙሉ የሚቀይሩ ይሆናሉ።
ተፈጥሮ ያደለቻትን ጸጋዎች ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት አረንቋ በማውጣት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚገባውን የብልጽግና ደረጃ እስኪያገኝ ድረስ ትጋት የተሞላበት የልማት ምዕራፍ ተከፍቷል።
ከዚህ ስኬት ጀርባ ያለው ዋነኛው ሚስጥር ራዕይን ወደ ተግባር የሚቀይር ጠንካራ እና ቁርጠኛ አመራር ነው። በቻይናም ሆነ በሲንጋፖር ዕድገት ውስጥ እንዳየነው ከላይ እስከ ታች ባለው የአመራር እርከን የቅርብ ክትትል ማድረጉ እና በየደረጃው ያለውን አስፈጻሚ አካል ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋቱ ለፕሮጀክቶቹ ፍጥነት ወሳኝ ድርሻ አለው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተመዘገቡት ድሎች እና የታዩት ውጤቶች እንደ መነሻ ሆነው የ2019 እና የቀጣዮቹ ዓመታት ጉዞ ኢትዮጵያን በሥራ የምትበለጽግባት፣ የታቀዱት ሥራዎች በላቀ አፈጻጸም የሚጠናቀቁባት እና ተስፋዎቿ ሁሉ ተጨባጭ የሚሆኑባት አገር ያደርጋታል።
እድገታችንን ለማስቆም የሚሞክሩ ኃይሎች የማይቻል ተራራ እንደገጠማቸው በተግባር የምናሳይበት ሀገራችንም የአፍሪካ የኢኮኖሚ እና የመሠረተ ልማት ማዕከል ሆና በጽኑ መሠረት ላይ የምትቆምበት ዘመን እውን እየሆነ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

20 days ago