በመደመር እሳቤ ላይ የተመሰረተው የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉዞ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመደመር ዕሳቤ መሠረት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባው የትናንትናውን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ሳይሆን፤ የትናንቱን በጎ እሴቶች ይዞ ዛሬ ላይ ያሉትን ስህተቶች አርሞ የነገውን አዲስ ተስፋ በመገንባት ነው።
ሀገረ መንግሥት ግንባታ ከዜሮ የሚጀመር ሳይሆን፤ የትናንትናውን ሙሉ በሙሉ በማፍረስ ፋንታ የትናንቱን መልካም ጅምሮችና በጎ እሴቶች ይዞ የሚቀጥል ነው።
በታሪክ ሂደት የገጠሙትን የሀገረ መንግሥት ስብራቶች በሳይንሳዊና በሰከነ መንገድ የመፍታት አካሄድ መከተል ያስፈልጋል፡፡
የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት እንዲሳካ የዜጎችና የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማቀናጀትን ይጠይቃል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር እሳቤ ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ እንደ ንድፈ ሐሳባዊ ማዕቀፍ የሚያገለግል ነው።
የሀገረ መንግሥት ግንባታን ለማሳካት የጋራ ማንነትን መገንባት፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማረጋገጥ እና ብሔራዊ እሴቶች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡
በሀገረ መንግሥት ግንባታ ብዝሃነትን በአግባቡ አለማስተናገድ እንደተግዳሮት የሚጠቀስ ሲሆን፤ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡
ከጫፍ እስከ ጫፍ በእኩልነት የምታድግ እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት፣ ሁሉንም ያለፈውን ታሪክ ማኅደር በአግባቡ ዘግቶ፣ በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት በመረዳት በጋራ ዓላማ ላይ መደመር አስፈላጊ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ያካሄደችው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ውስጥ ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ያረፈበትና ኢትዮጵያውያን ለሀገረ መንግሥት ግንባት ያላቸውን ፍላጎት ያሳዩበት ነው፡፡
በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ጸሐይና ዝናብ ሳይበግራቸው ረጅም ሰዓታትን በትዕግስት ተሰልፈው ድምጻቸውን በመስጠት ለሀገራቸው ሰላምና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል።
በምርጫው ወቅት ልጆቻቸው ጠንካራና ሰላማዊ ሀገር እንዲሁም ሀገረ መንግሥት ሊኖራቸው ይገባል የሚል የጸና አቋም የያዙ ኢትዮጵያውያን፤ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ድምጻቸውን በመስጠት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ፍላጎት በተግባር አሳይተዋል፡፡
በተጨማሪም በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የታየው የኢትዮጵያውን አንድነት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው፡፡
በምክክሩ ኢትዮጵያውን በመደማመጥ እና በመከባበር ስለ እናት ሀገራቸው በአንድ አዳራሽ መክረዋል፤ ዘክረዋል። ይበጃል ያሉትን በጎ ሐሳቦች በነፃነት አቅርበዋል። በዚህም ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡
በመጠፋፋት ላይ ተመስርቶ ለዘመናት የዘለቀውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል በመቀየር ሁሉንም የሚያሳትፍ የዴሞክራሲያዊ ባህልን መገንባት ይገባል፡፡
በዚህ ሂደት የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሁሉም ዜጋ ተሳትፎና ርብርብ ያስፈልጋል፡፡
ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሁሉንም ዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎና እገዛ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

21 days ago