ኢትዮጵያ በብሪክስ አባል ሀገራት ስለምን ተፈላጊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጀመረቻቸው የዲፕሎማሲ ስኬቶች መካከል የብሪክስ አባል መሆኗ ታላቅና ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን (በመቀጠልም ኢትዮጵያን፣ ግብጽን፣ ኢራንን እና ዩናይትድ አረብ ኤሚሬቶችን) ያቀፈው ይህ ስብስብ፤ የዓለምን የጂኦ-ፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መልክዓ ምድር ዳግም እየቀረጸ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ሀገሪቱ ከአህጉራዊ ተሰሚነቷ ባለፈ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ትንተና ዳይሬክቶሬት ባልደረባ የሆኑት ወንድሙ መኮንን፤ ‹‹Ethiopia and BRICS: Prospects and Challenges›› በሚል ርእስ በ‹‹Journal of Political Science and International Relations›› ዓለም አቀፍ የጥናት መድብል ላይ ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፋቸው፤
‹‹የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ቦታ፣ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ያላት የመሪነት ሚና እና እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅዕኖ ለብሪክስ ሀገራት ሳቢ አጋር አድርጓታል። ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ብሪክስ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰፊ መገኘት እንዲኖረው ከሚያደርገው ስትራቴጂ አካል አንዱ ነው፤ ይህም ኢትዮጵያ የምትገኝበት ይህ ቀጣና ለመካከለኛው ምስራቅ ካለው ቅርበት፣ ለቀይ ባህር መገኛ አካባቢ መሆኑና በቀጣናዊ ሰላምና ጸጥታን በማስጠበቅ ረገድ ካለው ከፍተኛ የሆነ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው›› ሲሉ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ለመሆን ስትወስንም ከራሷ ብሔራዊ ጥቅም ባሻገር አባላቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ስትራቲጂካዊ ጠቀሜታቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡
የብሪክስ አባል ሀገራት አጠቃላይ የኢኮኖሚ ምርት ከ28 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያለው በመሆኑ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው። በጋራ ከዓለም ህዝብ ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑትን የሚይዙ ሲሆን፣ ለዓለም አቀፉ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ትልቅ ድርሻ ያበረክታሉ።
በተጨማሪም አራት ተጨማሪ አባል ሀገራት ማለትም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በመጨመራቸው የብሪክስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አቅም የበለጠ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡ የዚህ ስብስብ አካል መሆን ለኢትዮጵያ በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛል።
የሩሲያው ሎባቼቭስኪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆነው ተመስገን ወ/ጻድቅ፤ ‹‹Ethiopia's Membership in BRICS: Opportunities and Challenges›› በሚል ርዕስ ባለፈው ግንቦት ወር ባሳተሙት ጥናታዊ ጽሑፍ የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ያለውን ፋይዳ በስፋት ዳስሰዋል።
ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ ሀገር በመሆኗ፣ የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና እና መግቢያ በር፣ ትላልቅ የልማት እቅድ በመተግበር ላይ የምትገኝ ሀገር በመሆኗ እና የቀጣናው መሪ መሆኗን በመቀጠሏ የብሪክስ አባል መሆኗ በአባል ሀገራቱ መካከል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር ያላት ቁርኝት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በ”ውቀት ልውውጥ ያሉ አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ባላት ፍላጎት የሚመራ ነው።
የብሪክስ ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተፅዕኖ ማሳደጋቸውን በቀጠሉበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ አዳዲስ ገበያዎችን ለማግኘት፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎቿ ላይ ፈጠራን ለማስፋፋት በዚህ ጥረት ውስጥ ስትራቴጂካዊ ቦታዋን ለመያዝ ትፈልጋለች።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ከብሪክስ ጋር መጣመር፤ በቀጣናዊ ውህደት፣ በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እና በዓለም አቀፍ ትብብር ላይ የሚያስከተለውን የተወሰነ አንድምታ የመረዳት አስፈላጊነት በመኖሩ ነው።
በኢትዮጵያ እና በብሪክስ መካከል ያለው ግንኙነት በተለይም በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም እንዳለው ያመላክታሉ።
የብሪክስ ሀገራት ባላቸው ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም እና በትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ባላቸው ልምድ፣ የኢትዮጵያን ታላላቅ የልማት ግቦች በመደገፍ ረገድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
በአፍሪካን ስተዲስ ሪቪው የታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ እንደተመላከተው፤ ቻይና እንደ ኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመሳሰሉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ እና የመሠረተ ልማት ዘርፎች ላይ ግንባር ቀደም ኢንቨስተር ሆና ወጥታለች።
በተመሳሳይ ህንድ የሀገሪቱን እያደገ የመጣ የሠራተኛ ኃይል እና የገበያ አቅም በመጠቀም በኢትዮጵያ የእርሻ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ናት።
ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ባለፈ በሌሎች ዘርፎችም ለምሳሌ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በክህሎት ማሳደግ እና በጋራ የምርምርና ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በኢኮኖሚ ዘርፍ ያለው ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እያደገ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ የማምረት አቅሟን ለማሳደግ እና በዋና ዋና ዘርፎች የእሴት ሰንሰለቱን ከፍ ለማድረግ ያለው ጠቀሜታ ጉልህ ነው።
በተረፈ ወርቁ

20 days ago