Logo
SeledaPost
የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩ

​የቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ  በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ።

​ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም።

በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም።

​በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል።

በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Seledadotio
Seledadotio
24 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.