#ethiopia
ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ እስከ 2 በመቶ ሊቆረጥ ነው።
የክልል መንግስታት ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ላይ ከዜሮ ነጥብ 5 በመቶ እስከ 2 በመቶ የሚደርስ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ መዋጮ የሚቆርጡበት አሠራር መዘርጋታቸውን ተሰምቷል።
ከሠራተኞች ደመወዝ የሚቆረጥ መዋጮ በረቂቅ ደረጃ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ በመጨረሻ በጸደቀው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር አዋጅ ላይ ግን ቀሪ መደረጉ ይታወሳል።
ክልሎች ለመሰብሰብ የወሰኑት መዋጮ ተመሳሳይ ሲሆን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግን ከሁሉም ከፍ ያለ መጠን ማለትም ከ1 እስከ 2 በመቶ ለመቁረጥ ወስኗል።
በተያያዘ ዘገባ፦ ዓለም ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በማሳደግ ላይ ያሉ አገራት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ ጫና ሳያደርጉ ገቢያቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን የፖሊሲ ጥናት ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።
ባንኩ የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ ከአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንጻር ያለው ድርሻ በታሪክ እጅግ ዝቅተኛው 7.5 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ አፈጻጸም፣ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 13 በመቶ አማካይ አጠቃላይ ገቢና በተለይም እንደ፦
-ኬንያ፣
-ሩዋንዳ እና
-ኡጋንዳ ካሉ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ባንኩ ጠቅሷል።
ለሀገሪቱ የታክስ ገቢ ማነስ፣ ሕገወጥ ንግድ፣ የታክስ ነጻ መብቶች መብዛትና በግብር አሰባሰብ መዋቅር ላይ ያሉ ድክመቶች ዋና ምክንያት ናቸው ተብሏል። ባንኩ፣ በሀገራት የመዋቅራዊ አቅም ምድብ፣ ኢትዮጵያን 'በቅድሚያ መሰረታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ሒደት' ምድብ ውስጥ እንደምትገኝ ገልጿል።
Seledadotio

21 days ago