በሀገር ግንባታ መንገድ ላይ የሚታየው የብርሃን ወጋገን
***************
በአዲስ ተስፋ እና በታላቅ ራዕይ ዋዜማ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ፣ አዲስ መንግስት ለመመስረት በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ ወደ አዲስ የልማትና የብልፅግና ከፍታ የሚያሸጋግሩ በርካታ መልካም እድሎችን፣ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እና የወደፊት ተስፋዎችን ሰንቆ መጥቷል።
ከሚሰሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከልም የኢነርጂና የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የኃይል አቅርቦት ከማረጋገጣቸው ባሻገር ለአህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር መንገድ የከፈቱ ናቸው።
በከተማ ልማት እና ግንባታ መስክ አዲስ አበባን እንደ አፍሪካ መዲናነቷ ውብ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ተስማሚ የማድረግ ስራ በከፍተኛ ፍጥነት በመከናወን ላይ ይገኛል።
በቱሪዝም ዘርፉ የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ደግሞ በመላ ሀገሪቱ የተፈጥሮ መስህቦችን በማልማት ለዘርፉ አዲስ ህይወት ዘርተዋል።
በቱሪዝም ዘርፍ እንደ ዋና የኢኮኖሚ ሞተር በታደሱትና አዲስ በተገነቡት የቱሪስት መስህቦች ምክንያት ዘርፉ የውጭ ምንዛሬ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዋነኛ ምንጭ እየሆነ መጥቷል።
የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው መስፋፋት እና በከተሞች የሚገነቡ ዘመናዊ ሆቴሎች ሀገሪቱን የአፍሪካ የቱሪዝም እና የስብሰባዎች ማዕከል እያደረጓት ነው።
ይህ ሪፎርም ለወጣቶች ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተጀመሩ ዲጂታል እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሀላፊነት ተጥሎበታል።
በስንዴ ልማት እና በሀገር ውስጥ ምርት የተመዘገበው ውጤት ሀገርን በምግብ የመቻል እና ወጪን የመተካት ተስፋን አጎልቶታል።
አዲሱ መንግስት እነዚህን የተጀመሩ ግዙፍ ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የህዝቦችን አብሮነት በመገንባት እና ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱን በማፋጠን ኢትዮጵያን ወደተሻለ የብልፅግና ማዕረግ ያሸጋግራታል ተብሎ በተስፋ መንገድ የተስፋ ወጋገንን ያሳያል።
በልዩ እሸቱ

26 days ago