በአንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት በባህር ዳር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አንድ ልብ ለትውልድ በስሩ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል የትም ህርት ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት ከሚሰሩ ተግባራት መካከል በትምህርት ቁሳቁሶች እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን መቀጠል ለሚቸገሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ነው።
በዚህም መሰረት መስከርም 5 /2019 ዓም በባህር ዳር ከተማ ከ6ቱም ክፍለ ከተሞች ለተመረጡ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 100 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ተሰጧቸዋል።
በድጋፍ መስጠት ፕሮግራሙ ላይ የድርጅቱ መስራች እና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ማራናታ ተክለሰንበት ባደርጉት ንግግር ድርጅታቸው ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ትኩረት ሰጦ የሚሰራ መሆኑን በመግለጽ በዛሬው እለት በትምህርት ፕሮጀክታቸው አማካኝነት ለተማሪወች በተደረገው ድጋፍ አጅግ መደሰታቸውን በመግለጽ በቀጣይም በዚህ እና በሌሎችም ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመደገፍ ጠንክረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስፋፊያ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ስንታየው ተሾመ በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት በአንድ ልብ ለትውልድ የህጻናት የሴቶችና የአረጋውያን የድጋፍ ድርጅት አማካኝነት ለተማሪዎች የተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በትምህርት ዘመኑ መጀመረያ ላይ በወላጆች ለይ የሚፈጠረውን የኑሮ ጫና የሚያቃልልና ለተማሪወቹ ደግሞ መሠረታዊ የሆነውን ችግር የሚፈታ በመሆኑ ለተደረገው ድጋፍ ትልቅ ቦታ እንሰጠዋለን በማለት በከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዲይ መምሪያ እና ድጋፍ በተደረገላቸው ተማሪዎች ስም ድርጅቱን አመስግነዋል።

26 days ago