(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤርትራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በኢኮኖሚ፣ በነዳጅ ትብብር እና በተለይም በወቅታዊው የቀጠናው የደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማካሄዱ ተገለጸ። የህግደፍ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሀጎስ ገብረሕይወት እና የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ ነስረዲን መሐመድ ሳላህ የተካተቱበት ይህ የልዑካን ቡድን፣ ከሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ዋሊድ አል-ኩሬይጂ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዕድገት እና በቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ በስፋት መክረዋል።
ይህ የኤርትራ ልዑክ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትሩን ከማግኘቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ፣ ከሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ (ኃይል) ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም በዓለም ላይ ግዙፍ ከሆነው የሳዑዲ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ (ARAMCO) ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቶ ተጨባጭ በሆኑ የጋራ የኢኮኖሚ ትብብሮች ዙሪያ መወያየቱን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስታውቀዋል።
ከዚህ የኢኮኖሚ እና የነዳጅ ትብብር ጀርባ ያለው ትልቁ ወቅታዊ ጉዳይ ግን በቀይ ባህር ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት ነው። በየመን የሚገኙት እና በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች በቀይ ባህር በሚያልፉ ዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ላይ እያደረሱት ያለው ተከታታይ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት፣ የሳዑዲ አረቢያን የነዳጅ ንግድ (በተለይም የአራምኮን የወጪ ንግድ) ክፉኛ እያሰጋው ይገኛል። በመሆኑም ሪያድ ከየመን ትይዩ ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የቀይ ባህር ጠረፍ ያላትን ኤርትራን በነዳጅ እና በኢኮኖሚ ድጋፍ ከጎኗ ማሰለፍ፣ የሁቲዎችን ጫና ለመቋቋም እና ምዕራባዊ የቀይ ባህር ወገቧን ለማስጠበቅ የምታደርገው ወሳኝ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።
ይህ የኤርትራ ልዑካን በሳዑዲ አረቢያ እያደረገ ያለው ጉብኝት፣ በቀይ ባህር ቀጠና እየተካሄደ ያለውን አዲስ የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽሚያ አካል ነው። ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ በሶማሊያ ወታደሮችን በገንዘብ ኃይል እያሰለጠነች መሆኑ መጋለጡን ተከትሎ፣ አሁን ደግሞ የሁቲዎችን የባህር ላይ ጥቃት ለመመከት ከኤርትራ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከሯ፣ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግንብ እየገነባች መሆኑን ያረጋግጣል። ለኤርትራም ቢሆን የሁቲዎች ቀውስ ትልቅ የድርድር አቅም ፈጥሮላታል፤ አስመራ ያጋጠማትን የኢኮኖሚ እና የነዳጅ አቅርቦት ማነቆ ለመፍታት፣ ስትራቴጂካዊ መልክዓ-ምድሯን ለኃያላኑ የባህረ-ሰላጤው ሀገራት በከፍተኛ የኢኮኖሚ ዋጋ እየለወጠች ይገኛል።

23 days ago