Logo
YenetaTube
በፊፋ እና ካፍ ህግ መሰረት ብቸኛው እጩ አቶ ኢሳያስ ጅራ 50 ከመቶ ድምፅ ካላገኙ ምርጫው ይሰረዛል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፕሬዝዳንትነት ምርጫ ድምፅ መስጠት በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ይገኛል።

ለቦታው ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከጠቅላላው ድምፅ 50 ከመቶ ካላገኙ ምርጫው ተሰርዞ በድጋሚ እንደሚደረግ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሀይሉ ሞላ ገልጸዋል።

ምርጫው አንድ እጩ ብቻ የቀረበበት መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታና ስጋት የደቀነ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የምርጫ መመሪያ (Standard Electoral Code) ግን ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ ደንግጓል።

በነዚህ አለም አቀፍ ህጎች መሰረት አንድ ተወዳዳሪ ያለተፎካካሪ ብቸኛ እጩ ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ እንኳን ድምፅ መስጠት ሳያስፈልግ ወይም በቀጥታ አሸናፊ ተደርጎ አይሾምም።

በህጉ መሰረት ብቸኛው እጩ የጠቅላላ ጉባኤተኞቹን አብላጫ ድምፅ (50% + 1) የማያገኝ ከሆነ፣ ሂደቱ ውድቅ ተደርጎ አዲስ እጩዎች የሚካተቱበት ድጋሚ ምርጫ እንዲደረግ ይገደዳል።

ይህም አሰራር ድምፅ ሰጪዎች እጩውን የመቃወም እና ምርጫውን ወደ አዲስ ውድድር የመመለስ ሙሉ መብት እንዲኖራቸው የሚያስችል ነው።

በአሁኑ ሰዓት የፌደሬሽኑ አባላት ድምፃቸውን እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን፣ አቶ ኢሳያስ ጅራ አስፈላጊውን ድምፅ ማግኘት አለማግኘታቸው የታገደውን የምርጫ ሂደት ወደ አዲስ ውድድር የሚመልሰው ወይም የሚያጸናው ይሆናል።

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.