በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 861 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 861 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል አለ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን መካከል 485 ሴቶች 63 ህፃናት እንዲሁም 100 ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከ1 ዓመት በፊት በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ101 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

24 days ago