ፖል ዎከር ሊመለስ ይሆን?
#ethiopia | በታዋቂው የቪዲዮ ተከታታይ ፊልም ‘Fast & Furious’ ውስጥ ብሪያን ኦኮነር በመሆን የሚታወቀው ፖል ዎከር በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ቀደም ሲል ባልተለቀቁ ምስሎች አማካኝነት በ’Fast Forever’ ፊልም ላይ ዳግም ሊመለስ እንደሚችል የሚገልጹ ጭምጭምታዎች መደመጥ ጀምረዋል።
ይሁን እንጂ ዩኒቨርሳል ስቱዲዮስ ይህንን ፊልም ተመልሶ መምጣት በተመለከተ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ማረጋገጫ የለም።
በ‘Furious 7’ ፊልም ላይ የወንድሙን ምትክ ሆኖ የሰራው ኮዲ ዎከር አሁን ባለው የቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት እንደገና በአካል ተክቶ የመስራት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።
ነጠር ግን ለኮዲ ከቴክኖሎጂው በላይ ዋናው ነገር የፖል ዎከር ልጅ ሜዶው ዎከር ውሳኔ ነው። የአባቷን ገጸ ባህሪ በተመለከተ ማንኛውም አይነት ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት የሷ ፍላጎትና ፈቃድ ቅድሚያ መሠጠት እንዳለበት ያምናል።
ቪን ዲዝል የብሪያን እና የዶም ገጸ-ባህሪያት ለመጨረሻው ፊልም እንደገና እንዲገናኙ ፍላጎት እንዳለው ቢናገርም፣ የፖልን ገጸ-ባህሪ በከፍተኛ ክብር ከተሸኘበት ‘Furious 7’ በኋላ እንደገና ማምጣቱ ቀላል ውሳኔ አይደለም ብሏል።
ስለሆነም የፖል ዎከር በፊልሙ ላይ መታየት እንደ እድል የሚታይ እንጂ እስካሁን የተረጋገጠ አቅጣጫ አልያዘም።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

26 days ago