Logo
SeledaPost
የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን 24 ለሚጠጉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ የሰጠው የ12 ወራት የዕፎይታ ጊዜ መጠናቀቁን አስታወቀ

​ከትምህርት ጥራት ማሻሻያ (ሪፎርም) በፊት ከነበሩት 375 የግል ተቋማት ውስጥ 290ዎቹ ለድጋሚ ምዝገባ ያመለከቱ ሲሆን፣ 85ቱ ራሳቸውን አግልለዋል። እስካሁንም ያሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሙሉ እውቅና (Accreditation) ማግኘት የቻሉት ሦስት ተቋማት፣ ሦስት ካምፓሶች እና 17 የትምህርት ፕሮግራሞች ብቻ መሆናቸው ታውቋል።

​በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ በሚገኙ የግል ተቋማት ውስጥ 340,038 (አጠቃላይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች 41 በመቶ) ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይከታተላሉ።

የተቋማቱ ባለቤቶች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሆስፒታል መገንባትና የፒኤችዲ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ማሟላት አዳጋች መሆኑን በማንሳት ቅሬታቸውን ቢያቀርቡም፤ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አቢተው በትምህርት ጥራት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማይደረግ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

Seledadotio
Seledadotio
29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.