አቶ ክርስቲያን ታደለ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የመጀመሪያ መግለጫቸውን ሰጡ፤ «የጤና ሁኔታዬ ሲሻሻል እውነታውን በዝርዝር አሳውቃለሁ»
ለሦስት ዓመታት ያህል በእስር ላይ ቆይተው በበዓል ዋዜማ ከእስር የተፈቱት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ (ክሪስ)፣ ከእስር መፈታታቸውን ተክቶ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች «መሠረተ-ቢስ» መሆናቸውን በመግለጽ የጤና ሁኔታቸው ሲሻሻል እውነታውን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታወቁ።
የፓርላማ አባሉ ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሰጡት የመጀመሪያ አስተያየት፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት ከእሳቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጎን ለቆሙ ግለሰቦችና ተቋማት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅት የጤና ሁኔታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አቶ ክርስቲያን፣ ከእስር መፈታታቸውን አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሱ መረጃዎች መሠረት የሌላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
አክለውም የጤና ሁኔታቸው በተሻለ ሁኔታ ላይ ሲደርስ አጠቃላይ ሁኔታውንና እውነታውን ለሕዝብ በዝርዝር የሚያሳውቁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ለሦስት ዓመታት ያህል በእስር ላይ የቆዩት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ከአዲሱ ዓመት መባቻና ከበዓል ዋዜማ ጋር ተያይዞ ከእስር ከተለቀቁ በርካታ እስረኞች መካከል አንዱ መሆናቸው ይታወሳል።
Via ጉርሻ page

29 days ago