Logo
SeledaPost
AI የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል‼️
ከፍተኛ አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (#ai) ከሰው ልጅ አቅም በላይ ከደረሰና በቂ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጅ ህልውና ከባድ አደጋ ሊሆን እንደሚችል የAI ተመራማሪዎችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው።

#በአሜሪካዊው የAI ኩባንያ Anthropic የሚሰሩ ተመራማሪዎች ኃይለኛ AI በዚህ አስር ዓመት ውስጥ ለሰው ልጅ ህልውና አደጋ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

ከኩባንያው የለቀቀው ጃኮብ ኮክሰን የተባለ ተመራማሪ፣ AI እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ/ሊገድል የሚችልበት #እድል እንዳለ ሲገልጽ፣ አንድ የአሁኑ የAnthropic ተመራማሪም የዚህ አደጋ ዕድል ከ10 በመቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል።

እንደ የAI ተመራማሪዎቹ ገለጻ፣ እጅግ የላቀ AI ከሰው ልጅ ጥቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲሰራ የሚያረጋግጥ በቂ #የደህንነት ዕቅድ አሁን የለም።

ይህ ስጋት #በብሪታንያ ፓርላማም ተነስቷል። የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዝ ብራውን እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ስቱዋርት ራሰል፣ እጅግ የላቀ AI ከኑክሌር መሣሪያዎች ጋር ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ የሚበልጥ ለሰው ልጅ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ሆኖም ሁሉም ባለሙያዎች በዚህ ላይ አይስማሙም። የAI እና ማኅበረሰብ ባለሙያ ፕሮፌሰር ኬት ዴቭሊን እንደሚሉት፣ " AI የሰው ልጅን #ሊያጠፋ ይችላል " የሚለው ትንበያ የተረጋገጠ እውነታ ሳይሆን የአደጋ ግምት ነው።

በአሁኑ ወቅት እጅግ የላቀ " ሱፐር ኢንተሊጀንት " AI እንደሌለን እና መቼ እንደሚኖርም በትክክል መተንበይ እንደማይቻል ገልጸዋል።

ባለሙያዎች ግን AI የሚያስከትለው አደጋ የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ መጥፋት #ብቻ እንዳልሆነ ያስረዳሉ።

#የAI ስርዓቶች ለጎጂ ዓላማዎች መጠቀም፣ ሳይበር ጥቃት ማድረስ ወይም በሰው ስህተት አደገኛ ስርዓቶችን መቆጣጠር ከሚጠቀሱት አደጋዎች መካከል ናቸው።

በተጨማሪም የሐሰት መረጃ መስፋፋት፣ ሰው የሚሰራባቸውን ቦታዎች መተካት ፣ የግል መረጃ ደህንነት ስጋት እና AI ለማስኬድ የሚያስፈልገው ከፍተኛ ኃይል አሁኑ ወቅት እየታዩ ያሉ ችግሮችና ስጋቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።

አሁን ላይ " AI የሰው ልጅን ያጠፋል ወይ ? " ከሚለው ጥያቄ ባሻገር፣ እጅግ ኃይለኛ AI ከተፈጠረ በኋላ በሰው ልጅ ጥቅም ላይ እንዲውል ምን ዓይነት ቁጥጥር፣ ሕግና የደህንነት ሥርዓት መዘርጋት አለበት ? የሚለው አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
ዘጋርዲያን

Seledadotio
Seledadotio
29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.