የኢትዮጵያ ተጽዕኖ እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የብሪክስ ስብስብ አባል መሆኗ ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ በመክፈት በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖና ተደማጭነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
ኢትዮጵያ የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድ የነበራትን የረጅም ጊዜ ታሪክ መሠረት በማድረግ ወደዚህ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስብስብ የተቀላቀለች ሲሆን የውጭ ፖሊሲዋን በማጎልበት ረገድ ይህ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል የነበራትን የአንድ ወገን ጥገኝነት በመቀነስ የራሷን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ አዳዲስ የትብብርና የልማት አማራጮችን እንድትጠቀም መንገድ ጠርጎላታል።
በኢኮኖሚና በልማት ዘርፍ፣ የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ አዳዲስ የፋይናንስና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ፈጥሮላታል።
በተለይም ከአዲሱ የልማት ባንክ ጋር የሚደረገው ጥብቅ ትብብርና የባንኩ አባል የመሆን ሂደት ሀገሪቱ ያጋጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍና ለትላልቅ የመሠረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪና የኃይል ፕሮጀክቶች የፋይናንስ ድጋፍ እንድታገኝ ያስችላታል።
ከዚህ ባሻገር በአባል ሀገራት መካከል በሀገር ውስጥ ገንዘቦች የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በማስፋፋት ኢትዮጵያ የራሷን ጉልህ ድርሻ እንድትወጣ ያስቻለ ሲሆን ይህም የውጭ ንግዷን በማሳደግ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን በመጨመርና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን ረገድ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ ነው።
በአህጉር ደረጃም ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ የምሥራቅ አፍሪካና የአጠቃላይ አህጉሪቱ ጠንካራ ድምፅ ሆና እንድትወጣ አስችሏታል።
በታዳሽ ኃይል ልማት፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውይይቶች ላይ የራሷንና የአፍሪካን ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶች በማንጸባረቅ የአህጉሪቱን ዲፕሎማሲያዊ ክብደት በማሳደግ ላይ ትገኛለች።
በአጠቃላይ የብሪክስ ስብስብ አባልነት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላትን ሚና እንድታጎለብት ብቻ ሳይሆን፣ ለአዲሱና ፍትሐዊ ለሆነው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ አጀንዳ ቀራጭና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር እንድትሆን አድርጓታል።
በነገው ዕለትም በሕንድ መዲናዋ ኒው ዴልሂ መካሄድ በሚጀመረው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ኢትዮጵያን በመወከል ይሳተፋል፡፡
በአብረሃም አበራ

28 days ago