እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ፤ አሸጋገረን🙏
በዚህች ዓመት ተዋት፣ ወደ ፊት ግን ብታፈራ ደህና ነው… 🙏
ወርሃ መስከረም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መጀመሪያ መሆኑን ሰለጠነ ከሚባለው ዓለም የተለየ አቆጣጠጠር መከተላችንን በመመልከት ብዙዎች የተሳሳተ አካሔድ እንዳለን ያስባሉ፡፡ ይሁንና የመስከረም መባቻ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የቀደመ ዓመታቸውን አጠናቀው የቀጣዩን አዲስ ዓመታቸው ዑደት አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው፡፡ ቀንና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት የሚሆንበት የአዲስ ተስፋ ብስራትም ቀን ነው፡፡
አበቦች በምድር ላይ የሚፈኩበት፣ የደፈረሰው የሚጠራበት፣ ምድሩ ሁሉ የሚፈካበት የአዲስ ዓመት፣ የአዲስ ዘመን መለወጫ ነው መስከረም አንድ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ርዕሰ አውደ ዓመት ተብሎም ይጠራል፡፡ የሰው ልጅ ምሳሌ የሆኑት አበቦች ፈክተው አምረው መታየታቸውና ኋላ መርገፋቸው አምረን ደምቀን እስከወዲያኛው እንደማንቀጥል ማሳያ ነው፡፡ የምድር አበቦች እንዳበቡ በእምነትና በምግባር እንድናብብ ቤተክርስቲያን በሰፊው ታስተምረናለች።
ይህም በአንድ ወቅት በሃብት፣ በክብር ከፍብለን የምንታይበት ጊዜ እንዳለ ያሳየናል፡፡ አበቦቹ ሲረግፉ ዘራቸው በምድር ላይ እንዲቀር በሃብትና በክብር ከፍ ባልንበት ወቅት ቅድስት ቤተክርስቲያንን፣ ገዳማትና ገዳማውያንን በገንዘባችንና በጉልበታችን ብናስብ በሰማይ ቤት የሚተርፈን ዘር እንተዋለን፡፡ በ1ኛ ጴጥ 4፥3 “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።” ተብለናልና አዲስ መንፈሳዊ ለውጥም ያስፈልገናል፡፡
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ኹሉ ዝቅ ይበል፡፡ ጠማማውም የቀና መንገድ ይኹን፤ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይኹን፡፡ ሥጋም የለበሰ ኹሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ” ተብሎ በነቢዩ ኢሳይያስ የተጻፈውን እየሰበከ ነው የመጣው፡፡ ይሕ ስብከት አዲስ ዓመትን እንዴት ባለ ልብ መቀበል እንዳለብን የሚነግረን ነው፡፡ ተራራ ከሆነው ትዕቢታችን ወርደን ዓዘቅት ከሆነው የልብ ክፋታችንና ኃጢአታችን ወጥተን አዲሱን ዓመት ልንቀበለው ይገባል፡፡
በሉቃስ 13፥6-9፣ የአንዲት ለሶስት ዓመታት በወይን አጠገብ ተተክላ ያላፈራች በለስ ጌታ እንድትቆረጥ ሲያዝ፣ የወይን አትክልት ጠባቂው “በዚህች ዓመት ደግሞ ተዋት። ወደ ፊት ግን ብታፈራ ደህና ነው፤ ያለዚያ ግን ትቆርጣታለህ፡፡” እንዳለ፣ እኛም በቅዱሳኑ ፀሎትና ምልጃ ለዘንድሮ ደርሰን ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር የኛን እጅግ የበዛ በደልና ኃጢዓት ሳይቆጥርብን ዕድሜ ለንስሃ ሰጥቶ ካሸጋገረን፣ እኛም በአዲሱ ዘመን ከአሮጌነታችን በንስሃ የምንታደስበትና ፍሬ የምናፈራበት በጸሎት የሚያስቡንን ገዳማውያን አባቶችና መነኮሳት የምናስብበት ማስተዋል ያስፈልገናል።
ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 month ago