ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ዘመን እኛን ይመስላል - አዲስ ዓመት በአዲስ መንፈስ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ትናንትን ማደሻ፣ የአዲስ ነገሮች መነሻ ሁሌም ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ከመሆኑም ባሻገር ልዩ የሆኑ ነገሮች ሁሉ የሚጠበቁበት ነው - የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመት
የክረምቱ ወቅት አብቅቶ - መስከረም ሲጠባ፣ አሮጌው ዓመት አልቆ- አዲሱ ዓመት ሲጀምር፣ ምድር በብርሀን ትመላለች፣ በአደይ አበቦች ታጌጣለች፡፡
ሰውም እንደዚሁ የጨለማውን ወቅት ወደ ኋላ ትቶ፣ ዛሬን አቅዶ ነገውን ብሩህ የሚያደርግለትን ተስፋውን አንግቶ ሊራመድ ይነሳል፡፡
ኢትዮጵያ 2018ን በከፍታ አጠናቅቃ ዛሬ 2019 ዓመትን የተሻለ ብሩህ ለማድረግ አልማ ተስፋን ይዛ ወሃ መስከረም ቀን 1 ብላ ጀምራለች፡፡
ነገር ግን እውነተኛ ተስፋ እንዲሁ የሚሳካ ከንቱ ምኞት አይደለም ይልቁን የተገባ ተግባርን የሚፈልግ እንጂ!
አዲስ አመት የሚሰጠን ዕድል እንደ አዲስ መታደስን ፣ ቂምና ቁርሾዎችን በይቅርታ መፍታትን፣ ስብራቶቻችንን መጠገንን ነው፡፡
እንዲሁም ትናንት ዋጋ ካስከፈሉን ስህተቶች የምንማርበትን፣ ነገን ለማሻሻል የምንችልበትን ዕድል ሁሉ ጨምሮ ጨምሮ ይቸረናል፡፡
ታዲያ አዲሱ አመት ባመጣልን ዕድል ነገን አጥርተን ለመኖር ህሊናችንን ዝግጁ ማድረግ ከኛ የሚጠበቅ ሲሆን ሰላምና ደህንነታችንን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት ይፈልጋል፡፡
ሰላም ከሌሎች የሚሰጠን ሳይሆን በእጃችን ላይ ያለ የምንዘራው ዘር ነው፤ እያንዳንዱ ዜጋ በቃልና በተግባር በሚያሳየው የመቻቻል፣ የመከባበርና፣ የይቅር መባባል ተግባር ውስጥ የተሻለ ከዛሬ አልፎ ለነገ የሚተርፍ መልካም ዘርን ይዘራል፡፡
ሰላም፣ የይቅርታና ተስፋ በሚፈጥሩት ውህደት የዜጎች መረጋጋት ይረጋገጣል፤ ይህም በአንድ የጋራ ዓላማ ስር ለመሰለፍ ትልቅ መሰረት ነው፡፡
አዲሱ አመት የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን በጋራ ለመትከልና ለማደግ ሁለተኛ ዕድልን የሚሰጥ በመሆኑ ተስፋችን ፍሬን የሚያፈራው ካለፈው ትምህርት ወስደን ለነገ የሚበጅ የሰላም ዘርን ለመዝራት በሚኖረን ቁርጠኝነት ይሆናል፡፡
መልካም አዲስ ዓመት!

1 month ago