(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል 'ሲ-17' ግዙፍ የጭነት አውሮፕላን በዚህ የሳምንት መጨረሻ ለናይጄሪያ አየር ኃይል ልዩ ወታደራዊ ትጥቆችን እና ቁሳቁሶችን አድርሷል። ይህ የጦር መሣሪያ ርክክብ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሰውን "የውጭ ወታደራዊ ሽያጭ ስምምነት" አካል ሲሆን፣ የአሜሪካ እና ናይጄሪያን የሁለትዮሽ አጋርነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። ዕዙ አክሎም፣ ይህ ወታደራዊ ድጋፍ ናይጄሪያ በቀጣናው እያካሄደች ያለውን የጸረ-ሽብርተኝነት ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያግዝ አስታውቋል።
ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ ቀጣና፣ በተለይም ቦኮ ሃራምን ከመሳሰሉ አሸባሪ ቡድኖች ጋር ሰፊ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች። አሜሪካ ይህንን ወታደራዊ ትጥቅ ማቅረቧ፣ ዋሽንግተን በአፍሪካ ያላትን የጸጥታ እና የጂኦፖለቲካ ተጽዕኖ ለማስጠበቅ የምታደርገው ስትራቴጂካዊ ጥረት አካል ነው። በቅርቡ ከኒጀር እና ከሌሎች የሳህል ቀጣና ሀገራት ጦሯን እንድታስወጣ የተገደደችው አሜሪካ፣ አሁን ላይ ናይጄሪያን በቀጠናው ዋነኛ ወታደራዊ እና የጸጥታ አጋሯ አድርጋ ለመያዝ እየሰራች መሆኑን ይህ የጦር መሣሪያ ሽያጭ በግልጽ ያሳያል።
አሜሪካ በምዕራብ አፍሪካ ያጣችውን ወታደራዊ ተጽዕኖ በናይጄሪያ በኩል ለማካካስ ቆርጣ ተነስታለች! ይህ ወታደራዊ አጋርነት ለናይጄሪያ የጸረ-ሽብር ትግል ትልቅ አቅም የሚፈጥር ቢሆንም፣ በቀጠናው ላይ እየተካሄደ ያለውን የኃያላን ሀገራት የጂኦፖለቲካ ፉክክር ይበልጥ እንደሚያጦፈው ልብ ይሏል።

29 days ago