ተወዳጁ “ቆንጆዎቹ” መጽሐፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማነት ሊቀየር ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውና በብዙ አንባቢያን ዘንድ ልዩ ተወዳጅነትን ያተረፈው የደራሲ ሰርቅ ዳ. “ቆንጆዎቹ” የረጅም ልብወለድ መጽሐፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማነት ሊሸጋገር መሆኑን ሀገሬ ቴሌቪዥን አስታወቀ።
ከሦስት አሥርት ዓመታት በፊት ለንባብ የበቃውና በትውልድ ቅብብሎሽ እስከዛሬ ድረስ በሰፊው ሲነበብ የቆየው “ቆንጆዎቹ”፣ ከገጽ ወደ ስክሪን በመሸጋገር ለተመልካቾች በአዲስ መልክ ሊቀርብ ነው።
ሀገሬ ቴሌቪዥን ይህንን ተወዳጅ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ወደ ቴሌቪዥን ለማምጣት ከደራሲው ጋር የመብት ግዢ ስምምነት መፈጸሙን ገልጿል።
ጣቢያው እንደገለጸው፣ የመጽሐፉን ጥበባዊ ሀሳብ፣ ውበት፣ ስሜትና ጥልቀት በጥንቃቄ ጠብቆ ወደ ስክሪን ለማምጣት የዝግጅት ሥራዎች እየተካሄዱ ነው።
በተለይም ለሀገር በቀል የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ትኩረት የሚሰጠው ይህ ፕሮጀክት፣ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍና የስክሪን ጥበብ አፍቃሪዎች ልዩ የአዲስ ዓመት ስጦታ እንደሚሆን ሀገር ቴሌቪዥን ገልጿል።
የቀረጻ ሂደቱ፣ የተዋናዮች ምርጫ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ ይፋ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል።
“ቆንጆዎቹ”ን በአዲስ የስክሪን ዓለም ለማየት በቅርቡ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይጠብቁን!
ይትባረክ ዋለልኝ
#ቆንጆዎቹ #ሀገሬቴሌቪዥን #የኢትዮጵያሥነጽሑፍ #ethiopianliterature #ethiopiandrama

30 days ago