ኢትዮጵያን ለመገንባት የሳይበር ደኅንነትና የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው - በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያን ለመገንባት የሳይበር ደኅንነትና የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው አሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፡፡
ነገ የጳጉሜን 5 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ "የነገ ቀን" በሚል ስያሜ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሳይበር ሉዓላዊነትና የኢትዮ ኮደርስ ስኬቶችን በማሳየት እና አዲሷን ኢትዮጵያ በሚያመላክት መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ይውላል።
ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግና ብሩህ ተስፋ ያላትን አዲስ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሳይበር ደኅንነትና የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው።
ኢትዮጵያ በራሷ አቅም እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተጎናጸፈች እንድትሆን ለማድረግ ዛሬ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት መሠረት መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የጳጉሜን 5 ቀን "የነገ ቀን" በሚል ስያሜ የመንግስት አገልግሎት ሪፎርም፣ በሳይበር ሉዓላዊነትና ደህንነት፣ በሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት፣ በግብርና ትራንስፎርሜሽን እና የምግብ ሉዓላዊነት፣ በዲጂታል ክህሎትቶች ዙሪያ ትኩረት ይደረጋል።
ከዚህ በተጨማሪ የፈጠራ ምህዳር እና የስራ ዕድል፣ በምግብ ሉዓላዊነትና የአደጋ ስጋት መከላከል እንዲሁም የኢትዮጵያ ማንሠራራት በዕለቱ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች መሆኑን ተናግረዋል።
በሳይንስ ሙዚየም የሚካሄደው ይህ ዝግጅት የፓናል ዉይይቶች እና የተለያዩ የሚጎበኙ ሁነቶች የተዘጋጁበት መሆኑን ያመለክታል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት

1 month ago