(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዱባይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዲኤንኤ ማስረጃ ቢቀርብለትም የአባትነት ጥያቄን ውድቅ አደረገ፡፡ ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው አንዲት ሴት ለልጇ አባት እንዲሰየም ያቀረበችው ጥያቄ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ሆኗል፡፡ ይህች ስሟ ያልተጠቀሰው ሴት አባት እንዲሆን የጠየቀችው ወንድ የዲኤንኤ ምርመራ ምርመራ ተደርጎለት ባዮሎጂካል ወላጅ መሆኑ ቢረጋገጥም ፍርድ ቤቱ ግን ጥያቄዋን እንዳልተቀበለው ዘገባው አስረድቷል፡፡
እንደዘገባው ያስገባችው ማመልከቻ ልጁ በአባቱ ስም እንዲጠራ የሚል ሲሆን ይህንን ተከትሎ ህጋዊ የቀለብና መሰል ወጪዎችን አባቱ እንዲሸፍን የሚጠይቅ ነበር፡፡ ከሳሿ ለፍርድ ቤት እንደገለፀችው ሰውየውና እሷ ሚስጢራዊ የፍቅር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ይህንን ተከትሎ ልታረግዝ ችላለች፡፡ ልጁን ከወለደች በኋላ ሰውየው አባትነቱን ማመን ባለመቻሉ የተመዘገበው በእሷ ስም ብቻ በመሆኑ የአባቱ ስም ተመዝግቦ በስሙ እንዲጠራም ጠይቃ ነበር፡፡ ሰውየው ይህን የቀረበበትን ክስ በመቃወም የዲኤንኤ ምርመራ ብቻውን የዘር ሀረግነት ባለቤትነትን እንደማያረጋግጥ ገልፆ አባት ለመሆን የጋብቻ ግንኙነትን የሚያረጋግጥ ሰነድ መቅረብ እንዳለት ተከራክሯል፡፡
ጠበቆቹም በሁለቱ መካከል መደበኛም ሆነ መደበኛ ያልሆነ ጋብቻ እንዳለ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ እንዳልቀረበ ቢያንስ የሰው ምስክሮች እንኳ የሌሉ መሆናቸውን በመግለፅ መሟገታቸውን ከዘገባው ተመልክተናል፡፡ ይሁንና የታችኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የዲኤንኤ ምርመራው በሚገልፀው መሰረት ሰውየው በአባትነት መሰየም እንዳለበት ውሳኔ አሳልፈው ነበር፡፡ እንደዘገባው ሰውየው በእነዚህ ውሳኔዎች ቅር በመሰኘት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት የታችኛው ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሽሯል፡፡ እንደዘገባው የዱባይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በውሳኔው የዲኤንኤ ምርመራው ውጤት ጥንዶቹ የልጁ ወላጅ መሆናቸውን እንደሚገልፅና ይህም አባትና እናት መሆናቸውን እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡
ነገር ግን እሷ ከተናገረችው በመነሳት ልጁ የተወለደው ከህጋዊ ጋብቻ አለመሆኑን የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ከመንግስታዊ ተቋማት በቀረበ ሰነድ ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መመስረቷ መታወቁን አስረድቷል፡፡ ውሳኔው ጨምሮም ‹‹የልጁን የአባትነት መብት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ህጋዊ መስፈርቶች እስካልተሟሉ ድረስ የዲኤንኤ ምርመራ ውጤት ብቻውን የዘር ሀረግን ለመለየት አያስችልም›› በማለት አስታውቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በፌዴራሉ የወንጀል ህግ ቁጥር 41 አንቀፅ 90 መሰረት በልጅ የዘር ሀረግ ላይ በወላጆች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ፍርድ ቤቶች የዲኤንኤ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዝ እንደሚችሉ ገልፆ ይሁንና እንደዚህ ያሉ ውጤቶች መቼ ሊታመኑ እንደሚችሉ ሁኔታዎችን ማስቀመጡን ጠቅሷል፡፡ ስለዚህም ሴትየዋ ያቀረበችው የልጇ አባትነት በሰውየው እንዲሰየም የሚል ጥያቄ ውድቅ ሆኗል ሲል ዘገባው ገልጿል፡፡

1 month ago