Logo
YenetaTube
ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙት የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ዓለም አቀፉን የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ለመምራት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫ ዳግም እንደሚወዳደሩ የተቋሙ ቃል አቀባይ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በጎርጎሮሳዊው 2027 በሚካሔደው ምርጫ በድጋሚ እንደሚወዳደሩ በሚያዝያ ወር ማስታወቃቸውን ያስታወሱት የፊፋ ቃል አቀባይ “ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ኢንፋኒቲኖ በድጋሚ ለመመረጥ ይቀርባሉ” ብለዋል።
ፊፋ የ56 ዓመቱ ስዊትዘርላንዳዊ በድጋሚ ለፕሬዝደንትነት እንደሚወዳደሩ ያረጋገጠው ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰ ዕቅድ ካቀረቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ኢንፋንቲኖ በፊፋ መርሐ-ግብሮች የግል ኢንቨስትመንት ለማካተት “ፊፋ ፎርዋርድ ኢንተርፕራይዝ” የተባለ ተቋም ለማቋቋም የጀመሩት ውጥን ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው ነበር። ተሳክቶላቸው በድጋሚ ከተመረጡ እስከ ጎርጎሮሳዊው 2031 ፊፋን በፕሬዝደንትነት ይመራሉ።

DW Amharic

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.