Logo
YenetaTube
በ38 ማረሚያ ቤቶችቤተመፃህፍት ሊከፈት ነው
በአንድ ልብ ለትውልድ የሕፃናት፣ የሴቶችና የአረጋውያን መርጃ ድርጅት ከኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ተቋማት ኮሚሽን ጋር የ5 ዓመት የጋራ ትብብር ስምምነት ተፈራረመ።

የስምምነት ሥነ-ሥርዓቱ በአዳማ ድሬ 2 ሆቴል የተከናወነ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በ38 የማረሚያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የተለዩ ሦስት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ይተገበራሉ።
የተለዩት ፕሮጀክቶችም የሻሎም ቤተ-መጻሕፍት፣ “እኔም ለእህቴ” እና የሕፃናት ድጋፍ ፕሮጀክቶች ናቸው።

በዚሁ መሠረት፦
የታራሚዎችን እውቀትና ስብዕና ለመገንባት በሁሉም 38 ማረሚያ ተቋማት ቤተ-መጻሕፍት ይከፈታሉ።
ለ5,000 ሴት ታራሚዎች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴሶች ይሰራጫሉ።
በማረሚያ ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ 1,000 ሕፃናት ፍራሽ፣ ብርድ ልብስና የትምህርት ቁሳቁሶች ይቀርባሉ።

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ማራናታ ተክለሰንበት እንደገለጹት፣ ስምምነቱ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በማላቀቅ ለሀገራቸው ጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

የኦሮሚያ ክልል ማረሚያ ተቋማት ኮሚሽነር ሻፊ በበኩላቸው፣ የኮሚሽኑ ዓላማ ታራሚዎችን መቅጣት ብቻ ሳይሆን ማነጽና ማስተማር መሆኑን ጠቁመው፣ ፕሮጀክቱ ለዚህ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.