Logo
SeledaPost
ናይጄሪያውያን ወጣቶች ኩላሊታቸውን
በ1,000 ዶላር እየሸጡ ነው

"ኩላሊታችሁን ሳይሆን ሀሳባችሁን ሽጡ"

በናይጄሪያ በተከሰተው  የከፋ የኑሮ ውድነትና ድህነት ሳቢያ ወጣቶች ኩላሊታቸውን  በ1,100 ዶላር  እየሸጡ መሆኑ ተሰምቷል። የቀድሞው የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዚዳንት አቲኩ አቡበከር ይህን አሳዛኝ ሁኔታ በማንሳት ጥልቅ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የችግሩ መንስኤ እና ወቅታዊ ሁኔታ፡

*የምግብ፣ የትራንስፖርትና የቤት ኪራይ ዋጋዎች እጅግ መናራቸው ለዚህ ችግር ዳርጓቸዋል።

* ፖሊስ ሁለት የህክምና  ባለሙያዎችን ጨምሮ በአራት ግለሰቦች ላይ ህገ-ወጥ የሰዎች አካል ዝውውር ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

  ምንም እንኳን ሪፖርቶቹ ሙሉ በሙሉ ባይረጋገጡም፣ የኢኮኖሚ ቀውሱ የሰውን አካል እስከ መሸጥ ማድረሱ ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል።

የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት መልእክት፡  ወጣቶች መሸጥ የሚገባቸው አካላቸውን ሳይሆን የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን ሊሆን ይገባል ሲሉ አቲኩ አቡበከር አሳስበዋል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.