Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ እና ኢራን ወታደራዊ ፍጥጫ ጋር በተያያዘ የሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት፣ በዋሽንግተን እና በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። ትራምፕ ከኢራን ጋር ያለውን ግጭት “ቀላል እና እዚህ ግባ የማይባል” (small potatoes) ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የሰው ህይወት መጥፋቱንም ከቬትናም ጦርነት ጋር በማነጻጸር አሳንሰው አቅርበውታል። በቬትናም ጦርነት መቶ ሺህ አሜሪካውያን ሲገደሉ አሁን ግን የተገደሉት አስራ ስምንት ወታደሮች ብቻ ናቸው በማለት ያቀረቡት ንጽጽር፣ ዋጋ የተከፈለበትን የዜጎች ህይወት ለፖለቲካዊ ፍጆታ ማቅለል ተደርጎ ተወስዷል።

ትራምፕ የአሜሪካ ጥቃቶች "የተቆራረጡ" (መሆናቸውን በመግለጽ ውጥረቱን ለማርገብ ቢሞክሩም፣ በሌላ በኩል ግን የኢራንን ቁልፍ የኒውክሌር ማዕከላት ኢላማ ያደረገ ከባድ ወታደራዊ ዛቻ ሰንዝረዋል። በተለይም የኢራን የበለጸገ ዩራኒየም ይገኝባቸዋል የሚባሉ የመሬት ውስጥ ዋሻዎች ያሉት የፒክአክስ ማውንቴን ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል በይፋ ማስጠንቀቃቸው፣ ቀውሱ ከቀጠናዊ ግጭት ወደ አደገኛ የኒውክሌር አደጋ ሊሸጋገር እንደሚችል አመላካች ተደርጓል።

ይህ የትራምፕ ንግግር በአንድ በኩል የአሜሪካ መራጮችን ከጦርነት ስጋት ለማረጋጋት የግጭቱን መጠን አሳንሶ የማሳየት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቴህራን ላይ ፍጹም የበላይነት ለመያዝ የኒውክሌር መሠረተ ልማቶችን እንደ መደራደሪያ እና የማስፈራሪያ ካርድ የመጠቀም ስትራቴጂያዊ አካሄድ መሆኑን ተንታኞች ይገልጻሉ።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.