ሦስት የሪል እስቴት ተቋማት ''አማን ፕሮፐርቲስ'' በሚል አዲስ ስያሜ ወደ ገበያ ተቀላቀሉ
#ethiopia | ከአምስት ዓመታት በላይ በሪል እስቴት ዘርፍ ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ላፍቶ ላይፍ፣ ኒው ላይፍ እና ስካይ ቪው የተባሉ የሪል እስቴት ተቋማት በአንድ ብራንድ ስር ተዋህደው “አማን ፕሮፐርቲስ” በሚል ስያሜ ሥራቸውን ማስቀጠላቸውን የኩባንያው የኢቨንትና ፕሮዳክሽን ስፔሻሊስት ዳዊት በሪሁን ገለጹ።
እንደ ዳዊት በሪሁ ገለጻ፣ ሦስቱን ተቋማት ወደ አንድ በማምጣት አማን ፕሮፐርቲስን በተጠናከረ አቅምና ፋይናንስ ራሱን የቻለ ጠንካራ የሪል እስቴት ተቋም ለማድረግ ዓላማ ተይዟል። አዲሱ ብራንድም የተቋማቱን አቅም በአንድ ላይ በማሰባሰብ በገበያው ውስጥ የተሻለ አቅም እንዲኖረው የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል።
አማን ፕሮፐርቲስ በአሁኑ ወቅት በብስራተ ገብርኤል ላፍቶ ሞል አቅራቢያ፣ በብስራተ ገብርኤል ኦልማርት አካባቢ እና ከሳንፎርድ ኢንተርኮንቲነንታል ፊት ለፊት በሚገኙ ሦስት ሳይቶች ላይ ፕሮጀክቶችን እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
በቀጣይም ቦሌ ቻይና፣ ፒያሳ፣ተክለሃይማኖት፣ ቦሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ወደ አሥር የሚደርሱ ሳይቶችን ለማስጀመር ዕቅድ እንዳለውም አቶ ዳዊት ጠቁመዋል።
ከአዲሱ ብራንድ ማስተዋወቅ ጋር ተያይዞም ከነሐሴ 29 ጀምሮ በላፍቶ ሞል ግቢ ኤክስፖ እንደሚካሄድ ተነግሯል። በዓልና አዲስ ዓመትን አስመልክቶ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ በማዘጋጀት የተለያዩ አፓርትመንትና ሬዚደንሻል ፕሮጀክቶችን ለሽያጭ ለማቅረብ መዘጋጀቱን አማን ፕሮፐርቲስ ገልጿል። በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በኤክስፖው እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
ኩባንያው በግንባታ ሂደቱ የሚጠቀመውን ቴክኖሎጂ ለማሻሻልም ከጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ለመስራት ዕቅድ መኖሩን ዳዊት በሪሁን አስረድተዋል።
ይህም በግንባታ ወጪና ሂደት ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስ እና የግንባታ ሥራውን በተሻለ ቴክኖሎጂ ለማከናወን የታሰበ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ደንበኞች የሚከፍሉት ገንዘብ በየትኛው የግንባታ ሂደት ላይ እንደዋለ በዝርዝር እንዲከታተሉ የሚያስችል የዲጂታል ሲስተም እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
ሲስተሙ በአሁኑ ወቅት በልማትና በሙከራ ደረጃ ላይ ሲሆን፣ በቀጣይ ደንበኞች የከፈሉት ገንዘብ ከመስኮት እስከ በር እና እስከ ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ድረስ የት ላይ እንደዋለ በዝርዝር እንዲያውቁ ለማስቻል የታቀደ ነው። ይህም በደንበኛና በተቋሙ መካከል ያለውን እምነት ለማጠናከር የታሰበ አሰራር ነው።
አማን ፕሮፐርቲስ ከሪል እስቴት ማህበሩ ጋር በመተባበርም በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በሽያጭና በሪል እስቴት አስተዳደር ዘርፎች አዳዲስ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ ዕቅድ እንዳለው ተመልክቷል።
በዚህም የሪል እስቴት ዘርፉ እንዲሻሻልና እንዲያድግ የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል።
በላፍቶ ያለውን ፕሮጀክት በተመለከተ ደግሞ ሥራው አዲስ የተረከበ ፕሮጀክት በመሆኑ የመላኪያ ጊዜው በቀጣይ ከደንበኞች ክፍያ መሰብሰብና የፕሮጀክቱን አቅም በማጠናከር እንደገና የሚወሰን መሆኑን አቶ ላይት ገልጸዋል። እስካሁን የፕሮጀክቱ ሥራ በድርጅቱ አቅም እየተከናወነ መሆኑንም ጠቁመዋል።
📸 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago