Logo
YenetaTube
በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች የአእምሮ ጤና እና በወጣቶች የሥራ ዕድል ላይ ያተኮረ አዲስ ስራ ተጀመረ

ግሪን ማይንድ ኔክሰስ ከማይንድ ዘ ማይንድ ጋር በመተባበር በአእምሮ ጤና፣ በአረንጓዴ ትራንስፖርት እና በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

"ሰላም ለአሽከርካሪው፣ ሥራ ለወጣቱ፣ ስምምነት ለመንገዳችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ በርካታ ዋና ዋና ነጥቦች ተገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ መኪና አሽከርካሪዎች መኪናቸውን ቻርጅ በሚያደርጉበት ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ "Harmony Road" እና "Coffee & Harmony" በተሰኙ ፕሮግራሞች የሥነ-ልቦና የመጀመሪያ እርዳታ እንዲያገኙ ይደረጋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ "Elite 30" ተማሪዎች የሁለት ወራት የሥልጠናና የመስክ ምርምር አጠናቀው ሰርተፊኬት ወስደዋል። ተማሪዎቹ ከ150 በላይ የኤሌክትሪክ መኪና አሽከርካሪዎች ጋር በመሆን የችግሮቻቸውን መንስኤ ያሰሱ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሥራና የኢንተርንሺፕ እድሎች እየተመቻቹላቸው ይገኛል።

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ወደ 200 ሺህ መጠጋቱ የተገለጸ ሲሆን፣ ባንኮች ብድር በሚሰጡበት ወቅት የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ስጋት ምዘናን መተግበር እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ ለዚህ አሰራር አስገዳጅ መመሪያ ማውጣት እንዳለበት ተመላክቷል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.