ኢትዮጵያ በዲጂታል ጉዞ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም ወደ ዲጂታል ዘመን በፍጥነት እየተሸጋገረች ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ይህን ለውጥ በማፋጠን አገልግሎቶቿን፣ ኢኮኖሚዋንና የዜጎቿን ዲጂታል ተጠቃሚነት እያሳደገች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ዲጂታል ለውጥ የሚመራው በተጠናቀቀው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እና አሁን እየተተገበረ ባለው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይ ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂን በኢኮኖሚ፣ በመንግሥት አስተዳደርና በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ በስፋት ለመተግበር ያለመ ነው።
የሰው ኃይልን ማብቃት፣ የዲጂታል ክፍተትን ማጥበብና ለፈጠራ እና ለኢንቨስትመንት ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር መፍጠርም ዋና የትኩረት አቅጣጫዎቹ ናቸው።
በዚህም ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ የዲጂታል መሠረተ ልማትና ተደራሽነት ላይ የታዩ ለውጦች የዲጂታል ለውጡን መሠረት የጣሉ ነበሩ።
የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያሳየው፣ እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ብቻ 7 ሚሊየን አዳዲስ የሞባይል ተጠቃሚ ዜጎች ተፈጥረዋል፤ የሞባይል ዳታ ዋጋም ከ2018 ዓ.ም. ጀምሮ ከ90 በመቶ በላይ ቀንሷል።
ከ2013 እስከ 2016 ዓ.ም. ደግሞ ቢያንስ 4 ሚሊየን ተጨማሪ ሰዎች የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመሆን የድጂታል ስርዓቱን ተቀላቅለዋል።
የዲጂታል ለውጡ አንዱ ቁልፍ መሠረት ፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ ሲሆን፣ ዜጎች የተለያዩ የፋይናንስና የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሠረተ ልማት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በዚህም አሁን ላይ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ወደ 50 ሚሊየን ገደማ መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል።
በሌላ በኩል የዲጂታል ፋይናንስ አጠቃቀምም በፍጥነት እያደገ ሲሆን፣ በ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ የተከናወነው የዲጂታል ግብይት መጠን 24 ነጥብ 2 ትሪሊየን ብር ደርሷል። ይህም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 12 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ አድጓል።
የ4ኛ እና 5ኛ ትቀውልድ ኔትወርክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች በመላው ሀገሪቱ 1200 ከተሞች የ4ኛ ትውልድ እንዲሁም 33 ከተሞች ደግሞ የ5ኛ ትውልድ ኔትውርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ዲጂታላይዜሽን የአገልግሎት ፍጥነትን ከማሻሻል ባለፈ አዳዲስ የንግድና የሥራ ዕድሎችንም እየፈጠረ ነው።
በዚህም እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ ከ3 ሺህ በላይ የዲጂታል ድርጅቶች ፈቃድ ማግኘታቸውን የዓለም ባንክ መረጃ አመላክቷል፤ እነዚህ ድርጅቶችም ከ24 ሺህ በላይ ቀጥተኛ የሥራ ዕድሎችን ፈጥረዋል።
በጥቅሉ፣ ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ዘመን የምታደርገው ጉዞ በመሠረተ ልማት፣ በዲጂታል ማንነት፣ በዲጂታል ክፍያ፣ በዲጂታል ክህሎትና በፈጠራ ላይ እየተመሠረተ ነው።
ዋና ዓላማውም ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን፣ አካታች፣ የተሻለ አገልግሎት፣ የበለጠ ዕድል፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችና የተሳትፎ አቅም ያለው ዲጂታል ማኅበረሰብ መገንባት ነው።
በአመለወርቅ ደምሰው

1 month ago