(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሶማሊያ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ አዌይስ ሀጂ ዩሱፍ፣ በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ድጋፍ የውትድርና ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አባላት ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መግባታቸውን አረጋግጠዋል። አማካሪው ወታደሮቹ ወደ ክልሉ የገቡት ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ በተሰጣቸው የዕረፍት ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ማረጋገጫ ከሶማሊያ ጋልሙዱግ ግዛት ሃናንቡሬ በተባለ ስፍራ ከአንድ ዓመት በላይ ስልጠና የወሰዱት ወታደሮች በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ በይፋ የተረጋገጠበት የመጀመሪያው ክስተት ነው።
"የፌደራል መንግስቱ ወታደሮቹ ለዚህ ዓላማ በክልሉ እንደሚገኙ ያውቃል፤ ሌሎች ጉዳዮች ካሉም ለሚዲያ እናሳውቃለን" ሲሉ አማካሪው መናገራቸውን ሶማሊጋርዲያን ዘግቧል። ይሁን እንጂ ይህ የመንግስት ማረጋገጫ የተሰማው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ ሚዲያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ወታደሮቹ ከድተው መግባታቸውን ከዘገቡ በኋላ ነው። ዘገባዎቹ እንደሚያመለክቱት፣ ስልጠናውን ከወሰዱት 3,000 ገደማ ወታደሮች መካከል በርካቶቹ ክደው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፣ በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ጅጅጋ ተወስደዋል።
የከዱት ወታደሮች ቁጥርን በተመለከተ የተለያዩ ሚዲያዎች ከ180፣ 300 እንዲሁም እስከ 900 የሚደርሱ የተለያየ አሃዞችን እያቀረቡ ቢሆንም፣ መረጃው በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም። በመሆኑም ወታደሮቹ በሶማሊያ መንግስት እንደተገለጸው በዕረፍት የገቡ ናቸው ወይስ ክደው የመጡ ናቸው የሚለው ጉዳይ እስካሁን በውል አልታወቀም። በናይሮቢ የሚገኘው የሳሃን ሪሰርች የአፍሪካ ቀንድ ተንታኝ፣ የደህንነት አማካሪው የሰጡትን ማረጋገጫ አድንቀው፣ ነገር ግን ሁኔታው "የሶማሊያ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተመለመሉት የኢትዮጵያ ፌደራል እና የክልሉ ባለስልጣናት እያወቁ ነው ወይስ አይደለም?" የሚል ተጨማሪ ጥያቄ እንደሚያስነሳ አስረድተዋል።
ይህ ክስተት የተፈጠረው ሞቃዲሾ እና አዲስ አበባ በፈረንጆቹ 2024 ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ውጥረት ውስጥ በነበሩበት ወቅት ነው። ምንም እንኳን ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፣ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መግባት በቀጣናው የደህንነት ጂኦፖለቲካዊ አሰላለፍ ውስጥ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ግንኙነት ላይ ሌላ ተጨማሪ ስሱ ጉዳይ ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል።

1 month ago