Logo
SeledaPost
በባህርዳር ከተማ የቀን ሰራተኛው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ዕድለኛ ሆነ

👉 ሽልማቱ ከወሎ ወደ ባህር ዳር ደርሷል

የባህር ዳር ነዋሪው ወጣት ኃይሌ እስከዚያው መኮንን በቆረጠው ቶምቦላ ሎተሪ በ4ኛ ዕጣ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ዕድለኛ ሆኗል፡፡

ወጣት ኃይሌ በቀን ስራ የተሰማራ ሲሆን አልፎ አልፎ ህይወቱን ለመቀየር ብዙ ሥራዎችን ይሞክር እንደነበር ገልጾ፤ ከነዚህም አንዱ እና ዋነኛው ሎተሪን መቁረጥ እንደነበር የገለጸ ሲሆን እድልና አጋጣሚ ገጥሞ እድለኛ አድርጎኛል በማለት ሽልማቱን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በተረከበበት ወቅት በደስታ ስሜት ውስጥ ሆኖ ገልጾልናል፡፡

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.