(ዘ-ሐበሻ ዜና) በበርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸውና በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው የሚታወቁት የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የስድስት ወር መታሰቢያ የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጸሎተ ፍትሐት እንደሚታሰብ ተገለጸ። በመርሐግብሩም የሟች ወዳጆች፣ ቤተሰቦችና በርካታ ምዕመናን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ክቡር ሥጋቸው ባረፈበት በካቴድራሉ ተገኝተው መምህሩን በጸሎት እንደሚያስቧቸው ታውቋል።
መምህር ዘላለም በሕይወተ ሥጋ በነበሩበት ወቅት በርካታ አርዓያነት ያላቸውን ማህበራዊና ሃይማኖታዊ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲያከናውኑ የቆዩ አባት ነበሩ። ከእነዚህም መካከል ከሦስት መቶ በላይ ለሚሆኑ አረጋውያን መደበኛ የምግብ ድጋፍ ማመቻቸት፣ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ሕፃናት ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ የሙሉ ጊዜ እንክብካቤ ማድረግ፣ እንዲሁም በሰበታ ከተማ የሚገኙ ከሰማንያ በላይ ዓይነ ስውራንን በማኅበር አደራጅቶ በቋሚነት መደገፍ በዋነኛነት ይጠቀሳሉ።
ከዚህም በተጨማሪ በገጠር አካባቢዎች አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ የሚታወቁ ሲሆን፣ አደባባይ ወጥተው መለመን የማይችሉ ችግረኛ ወገኖችን ያሉበት ድረስ በመሄድ በስውር ሲረዱ መቆየታቸው ይነገራል።
እኚህ ታላቅ መምህር በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ፣ የጀመሯቸው እና በአሁኑ ወቅት የምዕመናንን ድጋፍ የሚሹ ሦስት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ግንባታን ጨምሮ በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸውን በዘላቂነት ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። በመሆኑም ሥራዎቹን በአንድ ማዕቀፍ ሥር አቅፎ ለማስቀጠል የሚያስችል "የመምህር ዘላለም ወንድሙ የመታሰቢያ ድርጅት" የተሰኘ ተቋም በመቋቋም ላይ ሲሆን፣ በቅርቡም በይፋ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስተባባሪዎቹ አስታውቀዋል።
አስተባባሪ ኮሚቴው የመምህሩን ፈለግ በመከተል ምዕመናን የመንፈሳዊ አደራቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ ለበጎ አድራጎት ሥራዎቹ ማስቀጠያ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ወገኖች በጊዜያዊ ኮሚቴው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000751862192 ገቢ ማድረግ እንደሚችሉ አሳውቋል።

1 month ago