የአስመራ ነዋሪዎች በንጹህ ውሃ አጥረት
ምክንያት ቀይ ባህርን ለመጠጣት ተገደዋል ተባለ‼️
በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚኖሩ ዜጎች በከባድ የውሃ እጥረት ምክንያት የዕለት ተዕለት ህይወታቸው መስተጓጎሉንና ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ልብስ ማጠብ እና የንጽህና መጠበቂያ የሚሆኑ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለመጠበቅ ሲሉ የውሃ አጠቃቀማቸውን እጅግ ለመቀነስና አማራጭ የውሃ ምንጮችን በፍለጋ ለመንከራተት መገደዳቸውን ገልጸዋል።
የችግሩ አሳሳቢነት የከፋባቸው አያሌ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት መደበኛ የቧንቧ ውሃ ማግኘት ካቆመ ቆይቷል፤ በዚህም ምክንያት የውሃ ቦቴዎችን በመጠበቅ በውድ ዋጋ ውሃ ለመግዛት ተገደዋል። ሁኔታው ይበልጥ አሳዛኝ የሚሆነው ደግሞ አቅም በሌላቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ሲሆን አንዳንዶቹ የዝናብ ውሃ ለመሰብሰብ ሲጠባበቁ ሌሎች ደግሞ ከቀይ ባህር የሚጓጓዘውን የጨው ውሃ ለተለያዩ ፍጆታዎች ለማዋል እስከመገደድ ደርሰዋል።
ባለፈው ሐምሌ ወር የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በኤርትራ እየተባባሰ ለመጣው የውሃ አቅርቦት ችግር በምክንያትነት የተጠቀሱት የአየር ንብረት ለውጥ፣ የቆዩና የወደሙ መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ደካማ የውሃ አስተዳደር ስርዓት ናቸው።
ጥናቱ አክሎም በአሁኑ ወቅት የሚገኘው የውሃ አቅርቦት መደበኛ ያልሆነና ለጤና አስተማማኝ እንዳልሆነ በማስገንዘብ ሊከሰት የሚችለውን የጤና አደጋ ጠቁሟል።
ይህ ደረቅ ወቅቶች በመጡ ቁጥር ተደጋገሞ የሚከሰተው የውሃ እጥረት በነዋሪዎች የኢኮኖሚ አቅም ላይም የከፋ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የውሃ ግዥ ወጪ እየጨመረ መምጣቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ያላቸውን ትንሽ ገቢ ለውሃ እንዲያወጡ በማስገደድ ተጨማሪ የኑሮ ውድነት ፈጥሮባቸዋል።
አሁን ላይ በአስመራ እየታየ ያለው ይህ ቀውስ በከተማዋ ያለውን የዘለቀ የመሰረተ ልማት ውድቀትና የመሰረታዊ አገልግሎቶች ማጣት አጉልቶ የሚያሳይ አሳሳቢ ክስተት ሆኗል።
Seledadotio

1 month ago