Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወላጆች ለልጆቻቸው የፓስፖርት ማመልከቻ ሲያስገቡ የራሳቸውን የዜግነት ወይም የኢሚግሬሽን ማስረጃ ማቅረብን የሚያስገድድ አዲስ ረቂቅ ሕግ አቅርቧል። ይህ እርምጃ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ የትውልድ ስፍራን መሠረት ያደረገ ዜግነትን ለመገደብ እያደረጉት ያለው ጥረት አካል ነው። ረቂቅ መመሪያው ነሐሴ 6 ቀን የወጣውን እና "የልደት ቱሪዝም" የተሰኘውን ድርጊት ኢላማ ያደረገውን የፕሬዚዳንቱን አስፈጻሚ ትዕዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንዴት በሥራ ላይ ሊያውል እንደሚችል የሚያሳይ የመጀመሪያው ዝርዝር መረጃ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት በሰጡት መግለጫ፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአሜሪካን ዜግነት ትርጉም እና እሴት ለመጠበቅ ጽኑ አቋም እንዳላቸው እና የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱም ይህንኑ መስፈርት የሚያንጸባርቅ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የትውልድ ስፍራን መሠረት ያደረገ ዜግነትን መገደብ ፕሬዚዳንቱ በስደተኞች ላይ ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ውስጥ ቀዳሚው ጉዳይ ነው። ከዚህ ቀደም አውጥተውት የነበረው እና ከአንድ አሜሪካዊ ወይም ሕጋዊ ነዋሪ ለተወለዱ ልጆች ብቻ ዜግነትን የሚሰጠው ትዕዛዝ፣ የሀገሪቱን ሕገ መንግስት 14ኛ ማሻሻያ የሚጥስ ነው በሚል በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ6 ለ 3 ድምጽ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።

አዲሱ እና በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያተኮረው የነሐሴ 6ቱ አስፈጻሚ ትዕዛዝ፣ እናቶች ልጆቻቸው ዜግነት እንዲያገኙ በማሰብ ብቻ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ ወይም የልደት ቱሪዝምን ለመግታት ያለመ ነው። በዚህ መመሪያ መሠረት በአሜሪካ ውስጥ ለውጭ መንግሥት የሚሰሩ፣ ዜግነትን ለማግኘት በማጭበርበር ወይም በንግድ ልውውጥ የተሳተፉ፣ እንዲሁም ጠላት ተብለው የተፈረጁ ወላጆች ልጆች ዜግነት እንዳያገኙ ይከለከላሉ። ሕጉ ተግባራዊ ከተደረገ፣ ወላጆች ወይም ሕጋዊ አሳዳጊዎች የልጆቻቸውን የፓስፖርት ማመልከቻ ሲያስገቡ እንደ አሜሪካ ፓስፖርት፣ የልደት የምስክር ወረቀት፣ የኢሚግሬሽን ቅጽ ወይም የሕጋዊ ነዋሪነት ፈቃድ የመሳሰሉ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መረጃው ልጁ በአዲሱ ሕግ መሠረት ዜግነት ለማግኘት ብቁ መሆኑን ለመወሰን በመንግሥት ጥቅም ላይ ይውላል። በአሁኑ አሰራር ግን በአሜሪካ ለተወለዱ ልጆች ፓስፖርት ለማውጣት ወላጆች የወላጅነት ማረጋገጫ እና ፎቶግራፍ ያለበት መታወቂያ ማቅረብ ብቻ በቂ ሲሆን፣ ዜግነትን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ አይገደዱም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜግነታቸውን ሊያጡ በሚችሉ ሕጻናት ስም የክስ ሂደት የጀመሩ ጠበቆች፣ ይህ የትራምፕ አዲስ ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳይሆን ሁለት የተለያዩ የፌደራል ዳኞችን ጠይቀዋል። ከእነዚህ ክሶች አንዱ በዲሞክራቱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በተሾሙት የዲስትሪክት ዳኛ ዲቦራ ቦርድማን እየታየ ይገኛል። ዳኛዋ ዓርብ ዕለት በሜሪላንድ ግዛት በነበረው ችሎት በፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ ላይ ጥርጣሬያቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ከሳሾች ክሳቸውን እንዲያሻሽሉ እና ሕጉን ስለማገድ ውሳኔ ለመስጠት ጊዜ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል የፍትህ ሚኒስቴር ጠበቆች የፌደራል ኤጀንሲዎች ትዕዛዙን እንዴት እንደሚተገብሩ ይፋዊ መመሪያ እስካላወጡ ድረስ ክሱ ያለጊዜው የቀረበ በመሆኑ ሕጉን ማገዱ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.